2010-06-04 14:47:12

በዓለ ቅዱስ ቁርባን


ትላንትና የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በቫቲካን ከተማ በዓለ ቅዱስ ቁርባን አክብራ መዋልዋ ሲገለጥ፣ በኢጣሊያ እና በሌሎች አገሮች በሚገኙት የካቶሊክ አቢያተ ክርስያን በዓሉ እፊታችን እሁድ እንደሚከበር ተገልጠዋል። ቅዱስ ኣባታችን ትላትና በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ ባሲሊካ በዓሉን ምክንያት በማድረግ RealAudioMP3 መሥዋዕተ ቅድሴ አሳርገው ከቅዱስ ዮሓንስ ዘ ላተራኖ አደባባይ እስከ ሳንታም ማሪያ ማጆረ ባሲሊካ የቅዱስ ቁርባን ዑደት መምራታቸው ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለኛ ብሎ ስለ ፍቅር ህብስት በመሆን ለሁላችን የተሰጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን ማምለክ ማለት ትላትናም ዛሬም ጣኦት ከማምለክ ተግባር የሚገላግል፣ ጸረ የጣኦት አምልኮ ማለት መሆኑ በማስረዳት፣ በቅዱስ ቁርባን ፊት መንበርከክ ነጻነትን ማወጅ ማለት ሲሆን፣ ለጌታችን ኢየኡስ ክርስቶስ የሚሰግድ ምንም’ኳ ኃያላን ቢሆኑም ለማንም ምድራዊ ሥልጣን አይንበርከክም። እኛ ክርስትያኖች በዚህ ጥቀ ቅዱስ ምሥጢር ፊት ስንንበረከክ፣ በዚህ ቅዱስ ምሥጢር እወነተኛው እና ብቸኛው ዓለምን የፈጠረ አንድ ልጁች አሳልፎ እስከ መስጠት ያፍቀረን የእግዚአብሔር ኅላዌን እናውቃለን እናምናለንም ማለታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ይጠቁማል።

እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. ልክ ለእስራኤል ልጆች ከሰማይ እንደወረደው ማና ቅዱስ ቁርባን የዚህን ዓለም ምድረ በዳ ማለትም ከአገልግሎት እና ከፍቅር ይልቅ የሥልጣን እና ሃብት የማካበት ሹክቻ የተሞላበት የሞት ባህል የሚያስፋፉትን የተለያዩ የፖለቲካ እና የኤኮኖሚ ርእዮትን ለሚሻገረው እና እምቢ ለሚለው ለሁሉም እና ለማንኛው ዘመን ሰው ድጋፍ የሚሰጥ ወሳኝ እና አስፈላጊ ምግብ መሆኑ በማስረዳት፣ የቅዱስ ቁርባን በዓል ምንም’ኳ ውስጣዊ ጆሮአችን በልባችን በር ቆሞ ለሚያንኳኳው እግዚአብሔር ማዳመጥ የተሳነው ቢመስልም፣ ቅዱስ ቁርባን እግዚአብሔር በእኛ እንዲታወቅ ያደርጋል እንዳሉም መግለጫው ያስታውሳል።

በቅዱስ ቁርባን ተመርተን የምናደርገው ዑደት እርሱን እንደምንከተል እንመሰክራልን፣ ታሪካችንን እርሱ እንዲመራ እንጸልያለን፣ በብዙ የኅልውና ጥያቄ ምክንያት መልስ ለማግኘት የሚሰቃየውን ተመልከት፣ በዓለማችን ያለው እርሃብ፣ እርሱን የምግብ እጥረት እና የቀልብ እርሃብ እንጀራ ሆኖ ወደኛ በወረደው ሥጋህ እስወግድ፣ በሥራ ፍትነት ችግር ለተጠቁት፣ የሥራ እድል ያገኙ ዘንድ እርዳቸው፣ ብርሃንህን ስጠን፣ እራስህን ለእነርሱም ስጥ ቤተ ክርስትያንህን የውህደት ጸጋ አድላት የተከፋፈለውን ሕዝብህ አሰባስብ በማለት እ.ኤ.አ. 2006 ዓ.ም. በቅዱስ ቁርባን በዓል ወቅት ጸሎት ማሳረጋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.