2010-06-04 17:22:07

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ በቆጵሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝት ጀመሩ ፡


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ በቆጵሮስ ደሴት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ረፋድ ላይ ከሐዋርያዊ መንበራቸው ተነስተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ለኦናርዶ ዳ ቪንቺ አውሮፓላን ማርፊያ እንደደረሱ በፊኡሚቺኖ የፖርቶ ሳንታ ሩፊና ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጂኖ ረአሊ እና የቤተክርስትያን ከፍተኛ ባለስልጣናት ተቀብለው ሸኝቶዋቸዋል።

ቅድስነታቸው ከሶስት ሰዓት ተኩል በረራ በድሰኤቲቱ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኃላ አስራ አራት ሰዓት ላይ በምዕራባዊ ቆጵሮስ በምትገኘው ፓፎስ ከተማ ገብተዋል።

ፓፎስ አርባ ሺ ነዋሪዎች ያላዋት ትንሽ የቱሪስቶች መናርያ እና ወስብ ከምሆንዋ ባሻገር አርኬዎሎጂካዊት በተባበሩት መንግስታት በዩነስኮ የትምህርት የሳይንስ እና ባህል ተቋም ጥበቃ ስር ከሚገኙ የለማችን ከተሞች አንድ መሆንዋ ይታወቃል።

ይሁን እና ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፓፎስ ከተማ እንደገቡ በቆጵሮስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል የሐዋርያዊ ጉብኝቱ የፕሮቶኮል ሐላፊ አውሮፕላኑ ውስጥ ገብተው ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ሰላምታ አቅርበዋል።

ቅድስነታቸው ከአውሮፕላኑ እንደወረዱ የቆጵሮስ ደሴት ፕረሲዳንት ዲመትሪ ክሪስቶፊያስ ከባለ ቤታቸው በመሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ተቀብሎዋቸዋል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ እና የቆጵሮስ መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ዲመትሪ ክሪስቶፍያስ የቅድስት መንበር እና ቆጵሮስ ብሔራውያን መዝሙሮች አዳምጠዋል።

ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ወደ ቆጵሮስ የተጓዙ የቫቲካን መገናኛ ብዙኀን እንዳመለከትቱ ቅድስነታቸው አውሮፕላን ማረፍያ ላይ ሲጠባበቅዋቸው ከነበሩ የሃይማኖት ከፍተኛ መሪዎች ጋር ሰላምታ ተለዋውጠዋል።

የሃይማኖት መሪዎቹ ፡ ቅድስነታቸው ደሴቲቱን እንዲጐበኙ የጋበዙዋቸው የቆጵሮስ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ክሪስቶሞስ ፡ እና ተከታዮቻቸው ፡ በካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በኩል ፡ በቆጵሮስ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አብነ አንቶንዮ ፍራንኮ በደሴቲቱ የማሮናዊት ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጆሰፍ ሰይፍ ፡ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ፓትርያርክ ፎዓድ ጥዋል የቅድስት ሃገር ጠባቂ አባ ፒየርባቲስታ ፒጻባላ መሆናቸው መገናኛ ብዙኀን አስረድተዋል።

የቆጵሮስ ደሴት መሪ ፕረሲዳንት ዲሚትሪ ክሪስቶፍያስ ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የእንኳን ደህና መጡ ንግግር አድረገዋል

ፕረሲዳንቱ ንግግራቸው እንደፈጸሙ ፡ ቅድስነታቸውም ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፡ ክቡር ፕረሲዳንት ብፁዕ ፓትርያርክ ክሪስቶሞስ ብፁዓን እና ሊቀ ጳጳሳት እና ሲቪል ባለስልጣናት

ክቡርት እና ክቡራን በመጀመርያ ለተደረገልኝ ደማቅ እና ውንድማዊ አቀባበል ከልብ አመሰግናለሁኝ ፡

ፕረሲዳንት ክሪስቶፍያስ ቆጵሮስ ደሴት እንዲጐበኝ ላደረጉልኝ ጥሪ በማመስገን ለርስዎ እና ለቆጵሮስ ደሴት ህዝብ ከልብ ሰላምታ አቀርባለሁኝ ፡ በቅርቡ ቫቲካን እንደጐበኙ አስታውላሁኝ አሁን በድጋሜ መገናኘታችን ደስ ይለናል ፡ ካሉ በኅላ ቅዱስ አባታችን ርእሰ

ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ቆጵሮስ የሃይማኖቶች የባህሎች እና የታሪክ መገናኛ መሆንዋ ገልጠዋ። አያይዘው ረፓብሊክ ቆጵሮስ በቅርቡ የኤውሮጳ ሕብረት አባል መሆንዋ አስታውሰው ፡ ከሌሎች የኤውሮጳ ሕብረት ሀገራት አጋር በመሆን የርስ በርስ የመጠቃቀም ሂደት መጀመርዋ አመልከዋል።

የሕብረቱ አባል በመሆን ለደሴቲቱ ህዝብ ኤኮኖምያዊ እና ተክኖሎካዊ ጠቀሜታ እንዳለው ያወሱ ቕዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ፡የሕብረቱ አባል ሀገራት ፡ በበኩላቸው የደሴቲቱ መንፈሳዊ እና ባህላዊ እሴቶች ተቋዳሽ ሊሆኑ ይችላሉ ማለታቸው ተዘግበዋል።

ቆጵሮስ ደሴት በኤውሮፓ ኤስያ እና አፍሪቃ መሀከል ስለምትገኝ የባህሎች ከሁሉም በላይ ግን የውውይት ማእከል መሆንዋ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ጠቅሰው ከምተወድዋት ቆፕሮስ ከቤተሰቦቻችሁ እና ከ1ጐረቤታችሁ በከሃ ኩል እግዚአብሔር ጥበቃ በሰላም እና ደስታ ትኖሩ ዘንድ ምኞቴ ነው ብለዋል ። ቆጵሮስ ደሴት ሰሜን እና ደቡብ ተብላ ክ1974 ለሁለት እንደተከፈለች አይዘነጋም ።

ይሁን እና ቅድስነታቸው በእምነታችን ወላጆቻችን የሆኑ ቅዱሳን ጳውሎስ እና ባርኖባስ ቅዱስ ቃለ እግዚአብሔ ለመስበክ እና እሱን ለመገልገል በዚች ደሴት መኖራቸው እናስታውሳለን ያሉት ቅድስነታቸው የደሴቲቱ ህዝብ እና ካቶሊካዊ ማኅበረ ሰብ ለመጐኘት ዛሬ እዚህ መገኘቴ ብእጅጉ ደስ ይለኛል ማለታቸው ተመልክተዋል።

የቆጵሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝቴት በቅድስት ወላዲተ አምላክ እግዚእትነ ማርያም እና በቅዱሳን ጳውሎስ እና ባርኖባስ ጥበቃ እና እምነት እጠላለሁኝ በማለት ንግግራቸውን ፈጸመዋል።

ከዚህ በኃላ የወይራ ዛፍ ከባረኩ በኃላ ከየሃይምኖት እና መንግስት ባለስልጣናት ተሰናብተው ሃያ አምስት ርቆ ወደ ሚገኘው የቅድሰት ኪርያኪ ኪሪስቶፖሊቲሳ ቤተክርስትያን ተጉዘው ቤተክርስትያኑ ውስጥ ጸልየዋል ።

ቤተክርስትያኑ ለቀው በአቅራብያው ወደ ሚገኘው የፓፎስ ከተማ ተዘዋውረው ከከንቲባው ጋር ተገናኝተዋል።

በደሴቲቱ ሰዓት አቆጣጠር 16 ሰዓት ተኩል ሲሆን ከፓቮስ ከተማ በመኪና አንድ መቶ ስልሳ ኪሎሜትር በመጓዝ አሁን ዝግጅታችን በሚሰራጭበት ግዜ ርእሰ ከማ ኒቆሲያ ገብተዋል።

እዚያው በሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል መኖርያ የእራት ሥርዓተ ከፈጸሙ በኃል ለሊቱ እዚያው እንደሚያሳልፉት ተገልጸዋል።የቅድስነታቸው የቆጵሮስ ሐዋርያዊ ጉብኝት እስከ ፊታችን ሰንበት እንደሚዘልቅ ይታውቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.