2010-06-02 14:47:38

የር.ሊ.ጳ. የዕለተ ሮቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አጠቃላይ አስተምህሮ 02.06.2010


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት አሳርገው፣ ከመጽሓፈ ጥበብ ምዕራፍ 7 ከቁጥር 7 እስከ 10 “ስለዚህ ነገር ለመንኩ RealAudioMP3 እውቀት ተሰጠኝ፣ ለመንኩ ጥበብን የሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ አደረብኝ ከመንግሥት አገዛዝ ከዙፋኑም ይልቅ አከበርኋት፣ በእርሷ ዘንድ ሃብትን እንደ ኢምንት አደረጉኋት፣ ወርቅ ሁሉ በርሷ ዘንድ የተናቀ ነው በእርሷም ብር እንደ ጭቃ ነው፣ ዋጋ በሌለው እንቍ መሰልኋት፣ በደህንነት ከመኖር ከደም ግባትም ፈጽሞ ወደድኋት፣ ከእርሷ ከሚወጣ ብርሃን አይወሰንም አይጠፋምም ስለ ብርሃንም ፈንታ ትሆነኝ ዘንድ መረትጥኋት፣ ከእርሷ ጋር አንድነት እነዚህ ሁሉ ተድላ ደስታዎች መጡልኝ፣ ቍጥር የሌለው ባለ ጠግነት በእርሷ መጣልኝ፣ ይህች ጥበብ የእነዚህ ሁሉ አበጋዛቸው ናትና በሁሉ ደስ አለኝ። ከዚህ አስቀድሞ የእነዚህ ሁሉ አሳባቸው፣ ጥበብ እንደሆነ አላውቅም ነበር”።

የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በኤውሮጳ ዋና ዋና ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው በሰፊው የዛሬን ትምህርተ ክርስቶስ በጣልያንኛ ቋንቋ አቅርበዋል፣ የሚከተለውንም በእንግሊዘኛ በአጭሩ አስተምረዋል፦

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፤ በመሀከለኛው ክፍለ ዘመን የክርስትና ኣባቶች ትምህርት በማስደገፍ በጀመርነው የእለተ ሮብ ኣጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ መሠረት ዛሬ ሁለ ገባዊ ሊቅ ዶክተር ኮሙኒስ ተብሎ በሚጠራ ስለ ቅዱስ ቶማስ ዘእኵይኖ እንመለከታለን።

የቅዱስ ቶማስ ትምህርት ዘወትር በንባበ መለኮት ሊቃውንት እንደ ቀዋሚ ምሳሌ ይከበራል። ገና ወጣት ተማሪ እያለ በናፖሊ ዪኒቨርሲቲ ያኔ የተገኙት የኣሪስቶትል ጽሑፎች ጋር ተዋወቀ። የትምህርት ጊዜው በብዛት ስለ ኣሪስቶትል ትክክለኛ ትምህርት በማጥናት ኣሳልፈዋል። የፍላስፋው ጥሩ ነጥቦችን እና ትምህርቶችን በማጥናት ለክርስትያን ትምህርት ምንኛ ያህል ጥቅም አንዳለው ኣሳይተዋል። ቅዱስ ቶማስ የሰባክያን ማህበር ኣባል በመሆን የትልቁ ኣልበርት ትምህርትን በማጥናት በኮሎን በፓሪስ እንዲሁም በናፖሊ ንባበ መለኮትን ኣስተማረ። ብዙ የጥናት ሥራዎች ኣበርክተዋል፤ ከእነዚህ ስራዎች ትልቁ ሱማ ትየሎጂካ በማለት የሚታወቀው የቲዮሎጊያ መዝገብ፣ የቅዱሱ የእውቀት ስጦታ እንዲሁም ስለ እምነትና ኣእምሮ ስምምነትና ውህደት ያለውን ጽኑ እምነት ያሳያል። ቅዱስ ቶማስ ለበዓለ ቅዱስ ቁርባን ሥርዐተ ኣምልኮ የሚሆን ጽሑፍም ደርሰዋል፡ የዚህ የሥርዓተ ኣምልኮ ድርሳን ዜማዎች በቅዱስ ቁርባን ያለውን ጥልቅ እምነትና የነገረ መለኮት ጥልቅ ጥበቡን ያመለክታል። በሕይወቱ መጨረሻ ኣከባቢ ቅዱስ ቶማስ በመንፈሳዊ ኣስተንትኖ ብቃትን ኣግኝቶ ከእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ትልቅነት እና ከእውነተኛው ውበት ጋር ሲያወዳድረው እርሱ የጻፈው ሁሉ እንደ ሳር ከንቱ ሆኖ ስለታየው መጻሕፍ መድረስ ትቶ በኣስተንትኖ ብቻ ተጠመደ፡ ከሳምንት በኋላ በምናደርገው የዕለት ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ የዚሁ ትልቅ የንባበ መለኮት ሊቅ ትምህርትና ጽሑፎች እንመለከታለን ብለዋል።

በመጨረሻም በአደባባዩ ለነበሩና በረድዮና በተለቪዥን ለሚከታተልዋቸው በተለያዩ ቃንቃዎች ሲያመሰግኑ ሰሞኑ በጋዛ ሰርጥ ለዓመታት ተከበው በረኃብ እየተሰቃዩ ላሉት ፍልስጠኤማውያን የሚሆን እርዳታ ይዘው በዓለም ኣቀፍ የባሕር ክልል ሲጓዙ በእስራኤል ወታደሮች ጥቃት ለደረሳቸው የመንግሥት ያልሆኑ ከመላው ዓለም የተውጣጡ የግብረ ሠናይ ድርጅቶች ሠራተኞች ጉዳይ በተመለከተ፣ “በጋዛ ሰርጥ ኣቅራቢያ እየተፈጸመ ያለውን ኣሳዛኝ ሁኔታ በሥጋት እየተከታተልሁት ነው፤ ለኣውራጃው ሰላም የሚመኙ ሁሉ ልብ የሚሰልበው የዚህ ኣሰቃቂ ፍጻሜ ሰለባ ለሆኑት የተሰማኝን ሓዘን ለመግለጥ እወዳለሁ፤ ኣሁንም ሐዘን በተሞላው ልቤ እንደገና ለማለት የምፈልገው፤ ዓመጽ ክርክሮችን በማባባስ ኣሳዛኝ ድራማ በማስከተል ሌላ ዓመጽ እንዲወለድ ያደርጋል እንጂ ክርክር መፍትሔ ኣይደለም። ስለዚህ የአካባቢውን ሕዝብ የበለጠ ለሕይወት የሚበጅ ሁኔታ እንዲረጋገጥለት የሚያደርገው እውነተኛው መፍትሄ ከውይይት ብቻ እንደምገኝ፣ በኣከባቢ ደረጃና በዓለም አቀፍ ደረጃ ኃላፊነት ላላቸው የፖሊቲካ ባለሥልጣናት ጥሪ ለማቅረብ እወዳለሁ ካሉ በኋላ በአካባቢው እርቅ እና ሰላም እንዲረጋገጥ ካለ መታከት ጥረት ለሚያደርጉት ሁሉ በሚፈጽሙት ተግባር እግዚአብሔር ይደግፋቸው ዘንድ ተማጥነው፣ ብራኬ ሰጥተው ህዝቡን አሰናብተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.