2010-05-28 13:58:27

ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠሎምዮስ አንደኛ


ከባለፈው ቅዳሜ በሞስኮ ሓዋርያዊ ጉብኝት በማካሄድ ላይ የሚገኙት የቁስጥንጥንያ የአንድነት ፓትሪያርክ በርጠለሚዮስ አንደኛ ከትላትና በስትያን በሞስኮ እና በመላ ሩሲያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል አድነኛ ተሸኝተው ከሩሲያ ርእሰ ብሔር RealAudioMP3 ዲሚትሪ ሜድቨደቭ ጋር መገናኘታቸው ተገልጠዋል።

ግኑኝነት በተካሄደበት ወቅት በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስያን እና በሩሲያ መንግሥት መካከል ያለው ግኑኝነት አመርቂ እና አብነት መሆኑ በመጥቀስ አድንቀው መንግሥት እና ቤተ ክርስትያን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ እያስጨበጡ ነው ካሉ በኋላ፣ ለአገሪቱ የመጪው እድል ብሩህ የሚያደርግ ዜጎች በግብረ ገብ እና በሥነ ምግባር ታንጸው እንዲያድጉ የሚገፋፋ ብሎም የሩሲያ ባህል ክርስትያናዊ መሠረት ያለው መሆኑ የሚያረጋገጥ ነው እንዳሉ እንተርፋክስ ሬሊጀን የተሰኘው የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የሩሲያ ርእሰ ብሔር ሜድቨደቭ በበኩላቸውም በሁለቱ እኅታማቾች አቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው ግኑኝነት እና ውይይቱ እንዲጠናክር አደራ በማለት፣ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ በሩሲያ እየተረጋገጠ ያለው አወንታዊ ማኅበራዊ ባህላዊ ለውጥ ቀርበው በመገንዘብ ለሰጡት ምስክርነት በማመስገንም፣ ዓለማችን በተለያዩ ቀውሶች በተነካበት ወቅት ይህ ችግር ለመቀረፍ በሚደረገው ጥረት የአቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት አቢይ አስተዋጽኦ እንዳለው የማያጠራጥር ነው እንዳሉ የዜናው አገልግሎት አክሎ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.