2010-05-26 13:30:48

በሥነ አኃዝ የተራቀቀው የመገናኛ ብዙኃን እና የሕዝቦች መቀራረብ


ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ኡርባኒያኑም መንበረ ጥበብ ወቅታዊው በሥነ አኃዝ የተራቀቀው የመገናኛ ብዙሃን እና የሕዝቦች መቀራረብ እና ግኑኝነት በሚል ርእስ ሥር የተመራ አውደ ጥናት መከፈቱ RealAudioMP3 ተገልጠዋል።

በዚህ ጳጳሳዊ መንበረ ጥበብ የስነ መገናኛ ብዙሃን ጉዳይ የሚመለከተው የትምህርት ዘርፍ እንደተከፈትም በዚህ አጋጣሚም በይፍ ተገልጠዋል። የዚህ የአዲሱ የትምህርት ዘርፍ አቀነባበሪ እና አስተዳዳሪ ፕሮፈሶር ሉካ ፓንዶልፊ አውደ ጥናቱን በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የመገናኛ ብዙሃን በእደ ጥበብ መመንጠቁ አወንታዊ ነው፣ ሆኖም ግን ይኸንን እድገት ለምን እንደምንጠቀምበት እና እንዴት እንደምንገለገልበት መለየት እና ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፣ የህዝቦች ግኑኝነት እጅግ ፈጣን በማድረግ የመቀራረብ እድል ፈጥረዋል፣ ይህ መቀራረብ ግን የመገናኛ ብዙሃን ጉዳይ የሚመለከተው ሥነ ምግበር መሠረት በማድረግ ሰብአዊ ግኑኝነት እንዲሆን የሚደግፍ መሆን እንዳለበት በዚህ በሚካሄደው አውደ ጥናት ሰፊ ማብራሪያ ይሰጥበታል ብለዋል።

መገናኛ ብዙሃን መልእክት ናቸው፣ ስለዚህ የሚተላለፈው መልእክት ሥውር ዓላማ የሌለው ሆኖ የመገናኛ ብዙሃን የእውነት መሣሪያ መሆን አለበት ካሉ በኋላ፣ ይህ በሥነ አኃዝ የተራቀቀው መገናኛ ብዙኃን በኃላፊነት የሚተዳደር እና ክርስትያኖች ምስክርነት የሚያቀርቡበት ትብብር እና መደጋገፍ ለማረጋገጥ የሚያግዝ የተሟላ እድገት የሚያፋጥን መሆን አለበት በማለት የሚካሄደው አውደ ጥናት ይከንን ያሉትን በተለያዩ ርእሶች እንደሚተነትነው በማብራራት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.