2010-05-25 13:30:54

የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ


በቫቲካን የሩሲያ ሥነ ባህል እና ሥነ ሃይማኖት እለት ለሁለት ቀን በተለያዩ ዓውደ ጥናቶች እና በጋራ ውይይቶች ተሸኝቶ መታሰቡ ሲገለጥ፣ ዕለቱ እ.ኤ.አ. ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ቫቲካን በሚገኘው በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ፣ የሞስኮ እና የመላ ሩሲያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል አንደኛ ለቅዱስ አባታችን ክብር በሩሲያ ብሔራዊ ሙዚቀኞች አማካኝነት በካርሎ ፕኖንቲ ዩኒይር ተመርቶ በቀረበው የሙዚቃ ኮንሰርት አማካኝነት መጠናቀቁ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ የሙዚቃው ኮንሰርት ከመቅረቡም ቀደም በማድረግ ለሩሲያ ፓትሪያርክ የውጭ ጉኑኝነት ተጠሪ ሜትሮፖሊታ ሂላሪዮን አልፈየቭ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል አንደኛ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት መልእክት መነበቡም ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሙዚቃው ኮንሰርት እንዳበቃም፣ ንግግር ማሰማታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

ሙዚቃ ምሥራቅን እና ምዕራብን ዓለም ንጽጽር ውይይት እና መተባበር እንዲረጋገጥ የሚገፋፋ ያለፈውን እና ያለውን ባህል የሚያገናኝ ጥበብ መሆኑ የሚያብራራ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያሰሙት ንግግር የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በመግለጥ፣ የሩሲያ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል አንደኛ የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ተጠሪ ሜትሮፖሊታ ሂላሪዮን ባሰሙት ንግግር ሕይወት እና ቤተ ሰብ በሚመለከቱ ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ እንደነበርም አስታውሰው፣ ቅዱስ አባታችን በዚህ ተዛማጅ ብሎም አልቦ እግዚአብሔር ባህል መስፋፋት የሚያስከትለው ጉዳት መሠረታዊው የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብር እንዲካድ የሚገፋፋ መሆኑ በጥልቅ በማስረዳት ይህ ሁኔታ በኤውሮጳ አዲስ ሰብአዊነት እንዲረጋገጥ ምሥራቅ እና ምዕራቡ አለም ለውይይት የሚያነቃቃ ነው እንዳሉም ገልጠዋል።

በቫቲካን የተካሄደው የሩሲያ ሥነ ባህል እና ሥነ መንፈሳዊ እለት እንዲሁም የቀረበው የሙዚቃው ኮንሰር በሩሲያ ኦርቶዶስክ እና በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መካከል ያለው ግኑንኘት አመርቂ መሆኑ የሚመሰክር ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.