2010-05-21 14:04:48

ሬፓብሊካዊት መካከለኛ አፍሪቃ


የኡጋንዳ የጌታ አማጽያን ኃይሎች በመካከለኛይቱ ሬፓብሊክ አፍሪቃ ደቡባዊ ምሥራቅ ክልል ሠርገው በመግባት የሚፈጽሙት ጸጥታ የማወክ እና የአመጽ ተግባር ለመግታት የአገሪቱ የመከላከያ ኃይሎች ሰፊ RealAudioMP3 ጥቃት እየሰነዘሩ መሆናቸው ሲገለጥ፣ የክልሉ ሕዝብ የመንግሥት ወታደሮች የተያያዙት ጥቃት በክልሉ ጸጥታ እና ደህንነት ያረጋገጥ ዘንድ ያላቸውም ተስፋ ገሃድ ሲያደርጉ የቦንጋሱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኹዋን ኾሰ ውግዪረ ሙኞስ ተመሳሳይ መግለጫ መስጠታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት በማስታወቅ፣ ለክልሉ ጸጥታ እና መረጋገት ፈረንሳይ ወታደሮችዋ እንደምትልክ የዜናው አገልግሎት ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. ግንቦት 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት በክልሉ ካሰማራቸው ሠራተኞቹ ውስጥ ሁለት ሲገደሉ ሌሎች ሁለት የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ሲገለጥ፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኛች እና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው የበላይ ድርገት ከ መጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. እስከ ግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. የኡጋንዳው የጌታ ሠራዊት አመጽያን ኃይሎች በሃት ምቦኑ በጌረኪንዶ በቡተ በኪተሳ እና በሚስኪነ ክልል ሰፊ ጥቃት መሰንዘራቸው በመግለጥ፣ በሱዳን ደቡባዊው ክልል ጭምር ሠርገው በመግባት የሕዝቦች ጸጥታ እና ደህንነት እያናጉ መሆናቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.