2010-05-17 13:45:10

ኬንያ


የኬንያ መንግሥት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ለማሻሻል በሚል እቅድ መሠረት ያቀረበው ሰነድ የሕይወት ባህል የሚጻረር ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት መከበር የሚቀናቀንን የሕይወት ባህል ግድ የማይል፣ በኬኒያ የምስልምና RealAudioMP3 ሃይኖት ተከታዮች የሚከተሉት ቃድሂ በመባል የሚጠሩት ፍርድ ቤት ሕጋዊ እውቅና መስጠት የሚሉት ሀሳብ የሠፈረበት መሆኑ የኬኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በማብራራት፣ ይህ ጸረ ህይወት እና ማህበራዊ ሰላም ሊያደፈርስ የሚችል ሁሉም በሕገ መንግሥት ፊት እኵል መሆኑ የሚያመለክተው መመሪያ የማያከብር ጭምር መሆኑ በመጥቀስ ሕዝብ በሚሰጥው ውሳኔ እንዲቃወመው ጥሪ ማቅረባቸው ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰኘው የቅድስት መንበር እለታዊ ጋዜጣ ትላትና ባወጣው ኅትመቱ አመለከተ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአገሪቱ ያለው የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጤንነት ቀርቦ የሚገመግም በካቶሊክ ዓለማውያን ምእመናን ሥር አንድ እንቅስቃሴ መመሥረቱ ጋዜጣው ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.