2010-05-15 14:32:58

ቀጥተኛው የሰላም ውይይት በኢቀጥተኛ መንግድ ለማስጀመር


በመካከለኛው ምሥራቅ እልባት ያጣው ውጥረት እና ሁከት ለመግታት በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን የሚደረገው ጥረት ዳግም ለማስጀመር ባለፈው እሁድ በተባበሩት የአሜሪካም መንግሥታት ገላጋይነት መሠረት የፍልስጥኤም እና የእስራኤልም መንግሥታት ወኪሎች በተናጥል ከተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ልዩ ወኪል ጆርጅ ሚትቸል ጋር መገናኘታቸው ተረጋገጠ።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒ. ኔታንያሁ በኢቀጥተኛው መንገድ የሚደረገው የሰላም ድርድር የትም አያደርስም ስለዚህ በቀጥታ እና ፊት ለፊት ተገናኝቶ መደራደር ወሳኝ ነው እንዳሉ ሲገለጥ፣ ሁሉም በተለይ ደግሞ የመካከለኛው ምሥራቅ ውጥረት ተወናያን አገሮች በሚገባ የሚያውቁት እውነት ነው።

ባለፈው እሁድ ስለ ተካሄደው ኢቀጥተኛው የሰላም ውይይት በማስመልከት በቅድስት መሬት የቅድስት መንበር ቅዱሳት ሥፍራ እና ንብረት አስተዳዳሪ ኣባ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ኢቀጥተኛው የሰላም ድርድር የጋራ መተማመን አለ መኖሩ የሚመሰክር ነው በማለት ይህ የተካሄደው ኢቀጥተኛው የሰላም ድርድር ቀጥተኛው የሰላም ድርድር የሚያነቃቃ መሆን አለበት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.