2010-05-12 14:30:13

ቅድስት መንበር እና የቅድስት መንበር ዓለም አቀፍዊ ፖለቲካ


በቅድስት መንበር ለተለያዩ ልኡካነ መንግሥታት፣ ቅድስት መንበር እና የቅድስት መንበር ዓለም አቀፍዊ ፖለቲካ በሚል ርእሰ ጉዳይ በየዓመቱ ልኡከነ መንግሥታት ስለ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ታሪክ እና ተልእኮዋ፣ ሰውን ማእከል RealAudioMP3 ያደረገ የምታረማምደው አመለካከት፣ በዓለም አቀፍ እና በአገር አቀፍ ፖሊቲካ ጉዳይ የምትሰጠው አስተዋጽኦ እና የምታካሄደው ግኑኝነት በማህበራዊ እና በፖለቲካው መድረክ ያላት ሚና ምን እንደሚመስል ተጨባጭ እውቀት እንዲኖራቸው በሚል እቅድ፣ ጳጳሳዊ የግረጎሪያና መንበረ ጥበብ እና የዣክ ማሪታይን ተቋም በመተባበር የሚያዘጋጁት የትምህርት መርሃ ግብር መሠረት፣ ዘንድሮ ለየት ባለ መልኩ በቅድስት መንበር ለላቲን አሜሪካ አገሮች ልኡካነ መንግሥታ የሚሰጠው ትምህርት ከትላትና በስትያ በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የቤተ ክርስትያን ማንነት በሚል ርእስ ተመርቶ እየተካሄደ ሲሆን እስከ ግንቦት 16 ቀን እንደሚቀጥልም ለማወቅ ሲቻል፣ ቀጣዩ ትምህርት ከግንቦት 17 ቀን እስከ ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ተግባር በሚል ርእስ ተመርቶ በቶሪኖ ከተማ እንደሚካሄድም ተገልጠዋል። ትላትና በተካሄው አውደ ጥናት ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚካሄደው ግኑኝነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን እና በሆንዱራስ የተጉቺጋልፓ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲና ኦስካር አንድረስ ሮድሪገዝ ማራዲያጋ አስተምህሮ መስጠታቸው ተገለጠ።

ቤተ ክርስትያን የሰው ልጅ የተጋረጠበት አሳሳቢ ናቸው የሚባሉትን ጉዳዮችን ማእከል በማድረግ ከሁሉም አገሮች ጋር የምታካሂደው ግኑኝነት ማሳየል አስፈላጊ መሆኑ የገለጡት ብፁዕ ካርዲናል ዣን ልዊስ ታውራን አክለውም፣ ቤተ ክርስትያን እና ፖለቲካ በሚል ርእስ ሥር ሲያብራሩ፣ በዚህ ተዛማጅ ባህል እየተስፋፋ ባለበት ዘመን አማኞች የፖለቲካ አካላት እምነታቸውን በማኅበራዊ መድረክ በይፋ ሊኖሩት እንደሚገባ በማስረዳት፣ ብፁዕ ካርዲናል ሮድርገዝ ማራዲያጋ ልኡካነ መንግሥታት የቅድስት መንበር መዋቅሮች እና የቤተክርስትያን ታሪክ ተገቢ እና የተሟላ እውቀት ሊኖራቸው እንደሚገባ በማሳሰብ፣ የቤተ ክርስትያን የውስጠ አመራር ቅርጽዋ ምን እንድሚመስል አስረድተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.