2010-05-05 12:18:22

ከአምስት ዓመታት በፊት የመጀመርያ የበነዲክቶስ ሮብዓዊ ትምህርት ፡

 


ዛሬ ከአምስት ዓመታት በፊት ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ለመንበረ ሐዋርያ ጰጥሮስ ከተሰየሙ በኃላ ለመጀመርያ ግዜ ሮብዓዊ አስተምህሮ የሰጡበት ዕለት እና በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ተብለው እንዲጠሩ የፈለጉበት ምክንያት የገለጹበት ዕለትም የሚታውስበት ዕለት እንደሆነም ይታወቃል።

ሚያዝያ ሀያ ሰባት ቀን 2005 እኤአ ለመጅመርያ ግዜ ሮብዓዊ ትምህርት ሲሰጡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ተብለው እንዲሰየሙ የመሩጡበት ምክንያት ሲገልጹ ፡ ሁለት መቶ ስልሳ አራተኛ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በበዲቶስ አስራ አምስተኛ የኤውሮጳ ጠባቂ መኖራቸው እና የዓለም አንደኛ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንን የመሩ በመሆናቸው ይህንን ስም መረጥሁኝ ማለታቸው የሚታወስ ነው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ አምስተኛ የመጀመርያ የዓለም ጦርነት እንዲቆም ያካሄዱት ጥረት እና ጦርነቱ እንዳለቀም ዓለማችን ከጦርነት እና ከግጭት ነጻ ትሆን ዘንዳ ያካሄዱት ጥረት ፡ እግዚአብሔር ሰላሙ እንድያወርድ አብያተ ክርስትያናት ከምእመናናቸው ለጸሎት እና ለንስሐ መጥራታቸው በእጅጉ እንደሚያደንቁ ቅዱስ አባታን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ክአምስት ዓመታት በፊት ገልጠው ነበር።

ሰላም የእግዚአብሔር ስጦታ በመሆኑም እንዲታቀብ የዓለም ህዝቦች ሰላም እንዲሆኑ እና በመሀከላቸው ዕርቅ እንዲወርድ እመኛለሁኝ በማለት አያይዘው ማመልከታቸው አይዘነጋም።

እንደሚታወቀው ቅድስነታቸው ለመንበረ ሐዋርያ ጰጥሮስ ከመሰየማቸው በፊት ፡

ብፁዕ ካርዲናል ዮሴፍ ራትጺንገር ተብለው ይጠሩ መኖራቸው የሚታወስ ነው።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ከአምስት ዓመታት በፊት በቅዱስ ጰጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምእመናን ለመጀመርያ ግዜ ሮብዓዊ ትምህርት በሰጡበት ግዜ አያይዘው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክት እንዲሰየሙ የመረጡበት ሌላ ምክንያት ሲገልጹ ፡ በጀርመን በተለይ ባየርን ክፍለ ሀገር ቅዱስ በነዲክት ዘ ኖርቺያ በዓቢይ በዓል የሚከበር እና የሚዘከር ቅዱስ እና የኤውሮጳ ሕብረት መጣቀሻም የክፍለ ዓለሚቱ የክስርትና እሴትም ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የጀርመን ዜጋ መሆናቸው ይታወቃል።

ቅድስነታቸው ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጰጥሮስ ከመጠራታቸው በፊት በቅድስት መንበር የእምነት ዶክትሪን ማኅበር የበላይ ሐላፊ በመሆን ለበርካታ ዓመታት የሰሩ የንባበ መልኮት ጠቢብ መሆናቸው የሚዘነጋ አይደለም።

አያይዘውም የዓቢይ ቅዱስ ሐዋርያ ጰጥሮስ ተኪ እንዲሆን መመረጣቸው እንዳስገረማቸው እና እንዳስደነቃቸው ጠቅሰውም ትልቅ ሐላፊነት መሆኑ እና እግዚአብሔር ከሃሌ ኩሉ ዓለም እንድያግዛቸው እንደሚጠልዩ እና ምእመናንም በጸሎት እንዲሸኝዋቸው አደራ ማለታቸው አይዘንጋም ።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በመተካት ለመንበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጥሮስ መሰየማቸው የሚታወስ ሲሆን በነዲክቶስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዘክረው ፡ዓቢይ መንፈሳዊ መሪ እና ለቤተክርስትያን ከፍተኛ ሐዋርያዊ አገልግሎት የሰጡ ዓቢይ መንፈሳዊ ውርሻ ትተውልናል ሲሉ ማመልከታቸው የሚታወስ ነው።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ፡ በሳንምንት አንድ ግዜ ሮቡዕ ለምእመናን ትምህረት ቤተክርስትያን እንደሚሰጡ ሶስት ሐዋርያዊ መልእክቶች ለህዝበ ክርስትያን ማስተላለፋቸው አስራ አራት ዓለም አቀፍ







All the contents on this site are copyrighted ©.