2010-04-23 14:33:08

የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ምስክርነት እና ድረ ገጽ


በዚህ የሥነ ቅመራ እደ ጥበብ በመራቀቅ ላይ ባለበት ዘመን፣ ይኽንን መሣሪያ በመጠቀም የሚቀርበው ምሥክርነት ጉዳይ የሚመክር የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት የጠራው የአውደ ጥናት RealAudioMP3 ጉባኤ ትላትና መጀመሩ ተገለጠ።

ይህ የሥነ መገናኛ ብዙኃን ሊቃውንት የባህል ኣአካላትን ያሰባሰበው መድረክ፣ በዚህ የድረ ገጽ መስፋፋት እጅግ በጎላበት እና በማደግ ላይ በሚገኝበት ዘመን፣ የቤተ ክርስትያን ሚና እና በቤተ ክርስትያን ያለው የዚህ መሣሪያ አጠቃቀም ጉዳይ ምን እንደሚመስል ለማጤን ብሎም የዚህ መሣሪያ ጉዳይ የሚመለከት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለማቅረብ በሚል ስነ ኖልዎ ርእሰ ጉዳይ እንደሚወያይ ተገልጠዋል።

በዚህ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ሚላኖ በሚገኘው የካቶሊክ መንበረ ጥበብ የመገናኛ ብዙሃን ሥነ ማኅበራዊ ጉዳይ መምህር የሥነ መገናኛ ብዙኃን እና የሥነ ማኅበራዊ ጉዳይ ሊቅ ፕሮፈሶር ኪያራ ጃካርዲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስል፣ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል የድረ ገጽ ተጠቃሚነቱ እጅግ ከፍ ያለ ነው፣ መሣሪያው ለገዛ ራሱ የላቀ አወንታዊ እምቅ ኃይል ያለው ነው፣ ድረ ገጽ ልክ እንደ አንድ የትያትር መድረክ መሆኑ አስረድተው፣ ድረ ገጽ የሚፈጥረው የግኑኝነት አይነት ተጨባጭነት የሌለው ስለ ሚሆንም በሰዎች ዘንድ ያለው ሰብአዊው ግኑኝነት፣ ከሥውርነት ተላቆ ተጨባጭ መሆን ይገባዋል፣ የመገናኛ ብዙኃም መሣሪያ የሚያራርቅ ግኑኝነት ሥውር የሚያደርግ ከሆነ መሣሪያው ገዛ ራሱን ይጻርራል፣ ስለዚህ የመገናኛው መሣሪያ አገናኝነቱ መጣስ የለበትም፣ ቤተ ክርስትያን ይኸንን መሣሪያ ጉዳይ የሚመለከት የምትከተለው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ላይ ለየት ባለ መልኩ ያነጣጠረ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.