2010-04-21 16:01:56

የር.ሊ.ጳ. የዕለተ ሮቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አጠቃላይ አስተምህሮ 21.03.2010


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጲጥሮስ አደባባይ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት አሳርገው፣ ከግብረ ሐዋርያት ምዕራፍ 28:1 “በደኅና ከደረስን በኋላ በዚያን ጊዜ ደሴቲቱ ማልታ እንምትባል አወቅን። አረማውያንም የሚያስገርም ቸርነት አደረጉልን፤ ዝናብ ስለ ሆነም ስለ ብርዱም እሳት አንድደው ሁላችንን ተቀበሉን። ጳውሎስ ግን ብዙ ጭራሮ አከማችቶ ወደ እሳት ሲጨምር እፉኝት ከሙቀት የተነሣ ወጥታ እጁን ነደፈችው። አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው። ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም አሉ። እርሱ ግን እባቢቱን ወደ እሳት አራገፋት አንዳችም አልጐዳችውም፤ እነርሱም። ሊያብጥ ወይም ወዲያው ሞቶ ሊወድቅ ነው ብለው ይጠባበቁት ነበር ብዙ ጊዜ ግን ሲጠባበቁ በእርሱ ላይ የሚያስገርም ነገር ምንም ባላዩ ጊዜ። ይህስ አምላክ ነው ብለው አሳባቸውን ለወጡ።” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በኤውሮጳ ዋና ዋና ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው በሰፊው የዛሬን ትምህርተ ክርስቶስ በጣልያንኛ ቋንቋ አቅርበዋል፣ የሚከተለውንም በእንግሊዘኛ በአጭሩ እአስተምረዋል፦ “ውድ ወንሞቼና እኅቶቼ፦ባለፈው የሳምንት መገባደጃ ላይ የቅዱስ ጳውሎስ ጃልባ መስጠምና ለሶስት ወራት በማልታ የሰበከውን 1950ኛ ዓመት ማስታወሻ በዓል ለመሳተፍ ያደርጉት ጉብኝት የሚያስደስት ነበር። የሕዝብና የቤተ ክርስትያን ባለሥልጣናት ላደረጉልኝ ደማቅ አቀባበል ከልብ አመሰግንቸዋለሁ፣ ስለ የቅዱስ ጳውሎስ ስብከት በእነዚህ ደሲቶች እስከ ዛሬ ያስገኛቸው አመርቂ የእምነት ፍሬዎች የቅድስና ጉጉትና የሚያቃጥል የስብከተ ወንጌል ተልእኮ ቅናት በቅዱስ ጳውሎስ ዋሻ እግዚአብሔርን አመሰግሁ። በማልታ ሕዝብ ዕለታዊ ሕይወትና ባህል ጥልቅ ሥር የሰደደ የክርስትና ራእይ የዛሬውን ትላልቅ የኅብረተሰብና የሞራል ችግሮችን መጋፈጫ የሚሆን መፍትሔ መስጠቱን እየቀጠለ ነው። በማልታ ውስጥ ሕያው እምነት ገና እየጠነከረ መሆኑን አጉልቶ የሚያሳይ በቅዱስ ፑብልዩስ አደባባይ ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ሰፍኖ የነበረው ደስታ ራሱ ምስክር ነው። ማልታ በአቀማመጥዋ የብዙ አገሮች መገናኛ በመሆንዋ ከቀሪው ዓለም ተነጥላ አታውቅም፣ በሁሉም የማልታ ቦታ ሲያንበለብል ያየሁት የማልታ ልዩ መስቀልም የፍቅርና የዕርቅ ትክክለኛ ትርጉሙን አጥፍቶ አያውቅም።

እፊታችን ተደቅኖ ያለው የዘለዓለማዊው የወንጌል ጥበብና እውነት የማስተላለፍ ግዳጅ በልዩ መንገድ ወጣት ትውልድን ይመለከታል። በቫለታ ወደብ የማልታን ወጣቶች የቅዱስ ጳውሎስን መንፈሳዊ ጉዞ ተመልክተው እንደ ገዛ ራሳቸው ሞደል እንዲያደርጉት ሕይወታቸው ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ክርስቶስ በማግኘት እንዲለወጥ የእግዚአብሔር የፍቅር ዕቅድም ከማንኛውም ማዕበልና የጀልባ መስጠም እንደሚያይል እንዲያምኑ የግጥሚያ ጥሪ አቀርብኩላቸው። ካሉ በኋላ በዚሁ ሳምንት መዓርገ ዲቍና የተቀበሉ የጳጳሳዊ የእስኮትላንድ ኮለጅ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸውን ልዩ ሰላምታ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አብረዋቸው ለነበሩና በተለቪዥንና በረድዮ ለተከታተልዋቸው ምእመናን በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነው ሓዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት የዛሬውን ትምህርታቸው ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.