2010-04-20 13:52:42

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ 5ኛው ዓመት በመንበረ ጴጥሮስ ተልእኮ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለመንበረ ጴጥሮስ የተሾሙበት አምስተኛው ዓመት እ.ኤ.አ. ዛሬ ሚያዝያ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. መዘከሩ የቅድስት መንበር የማኅተም እና የዜና ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ RealAudioMP3 ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መገልጫ በመጥቀስ፣ ይህ የር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አምስተኛው ዓመት የመንበረ ጴጥሮስ ተከታይነት ጥሪ ምን እንደሚመስል ሲያብራሩ፣ ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው፣ የዛሬ አምስት ዓመት በፊት በሲስቲና ቤተ ጸሎት፣ ለጴጥሮሳዊ ኃላፊነት በመላ የካርዲናላት ጉባኤ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተመርጠው የታላቁ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ መንፈሳዊ ውርሻ በመቀበል፣ ለአሕዛብ በክርስቶስ አማካኝነት የተገለጠው እግዚአብሔር መሠረት በእግዚአብሔር እና በሰው ዘንድ ያለው ግኑኝነት በተለይም በቅዱስ ቁርባን የሚረጋገጠውን ግኑኝነት ማእከል በማድረግ ቅዱስ ቁርባ የቤተ ርክስትያን ማእከል መሆኑ እና የክርስቶስ ተከታይ ሕዝብ ዳግም ለማነጽ፣ በመደናገር እና በመጪው ሕይወት በመፍራትም መንገዱን ለመለየት ለተሳነው ሕዝብ ለመደገፍ፣ የሰው ልጅ መሠረታዊ ጥያቄ መልስ ማን መሆኑ ለማሳወቅ፣ እንዲሁም ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር ግልጽ እና መከባበር በተካነው መንፈስ ለመወያየት፣ የሚሉትን መንፈሳዊ እቅዶች የተሸኙ አመታት መሆናቸው እና ይህ ደግሞ በአውሽዊዝ፣ በኢስታንቡል፣ በኔው ዮር በሲድነይ በፈረንሳይ በአፍሪቃ በእየሩሳሌም ባካሄዱዋቸው ሐዋርያዊ ጉብኝቶች መረጋገጡንም ከገለጡ በኋላ በማያያዝ በተለያዩ ሃይማኖቶች የጸሎት ሥፍራ ዘንድ በመድረስ የሃይማኖቶች ግኑኝነትን የተዋጣለት ያደጉበት አመታት ነው ብለዋል። በመጨረሻም ርእሰ አቀንጹን ሲያጠቃልሉ፣ ስለ ፍቅር በጻፉዋት አዋዲት መልእክት ልማት ኤኮኖሚ በጠቅላላ በሥነ ምግባር የተካነ ተፈጥሮን እና ሰባአዊው ፍጡር የሚያከብር እንዲሆን የሰጡት አቢይት ትምህርት በማስታወስ፣ እግዚአብሔር እና ሕዝብን በማገልገል የሚቀጥል ጴጥሮሳዊ ተልእኮ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.