2010-04-14 14:12:56

በኮንጎ የጎማ ከተማ አዲስ ሊቀ ጳጳስ


በኮንጎ ዴሞክራሲዊት ሬፓብሊክ የሰሜናዊ ኪቩ ርእሰ ከተማ ጎማ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ተዮፊለ ካቦይ ሩቦነካ የክልሉ ቤተ ክርስትያን ለመምራት ከእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተሰጣቸው ሐዋርያዊ ኃላፊነት RealAudioMP3 ባለፈው እሁድ በጎማ ከተማ በሚገኘው ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አደባባይ በሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ጀምረዋል።

ቅዳሴውን መርተው ባሰሙት ስብከትም፣ ሰሜናዊ ኪቩ የአመጽ የጦርነት የወሲብ አመጽ በስፋት የሚታይባት ከተማ መሆኗ አብቅቶ፣ የሰላም እና የወንድማማችነት መንፈስ የሰፈነባት ከተማ ትሆን ዘንድ የሁሉም ተሳትፎ የሚጠይቅ የተቀደሰ ኃላፊነት ነው ብለዋል። የሰበካው ሊቀ ጳጳስ በመሆን ያገለገሉት ልሂቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋውስቲን ንጋቡ በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት መሳተፋቸውም ሲገለጥ፣ የርእሰ ብሔር ጆሴፍ ካቢላ ልኡካን በምክትል ጠቅላይ ሚኒ. የውስጥ ጉዳይ ሚኒ. ፕሮፈሶር ሉማኑ ብዋና ሰፉ የተመሩትም በቅዳሴው ሥነ ስርዓት ተገኝተዋል።

በዚህ አጋጣሚም ርእሰ ብሔር ካቢላ ለልሂቀ ጳጳጳስ ብፁዕ አቡነ ንጋቡ በክልሉ ሰላም ለማረጋገጥ የሰጡት አቢይ አስተዋጽኦ በማድነቅ፣ አዲስ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ለተሾሙት ለብፁዕ አቡነ ካቦይ ሬቦነካ ሰፉ መልካም ሐዋርያዊ ሥራ ተመኝተዋል።

ብፁዕ አቡነ ካቦይ ሬቦነካ ሰፉ እ.ኤ.አ በ 1941 ዓ.ም. የተወለዱ እ.ኤ.አ. በ 1972 ዓ.ም. የክህነት ማዕርግ ተቀበለው፣ እ.ኤ.አ. በ 1995 የኮሶንጎ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሹመው፣ እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. የጎማ ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ተሹመው እንዳገለገሉ ኣና ባለፈው ዓመት ጥቅምት ወር እዚህ በቫቲካን ተካሂዶ በነበረው በሁለተኛው የአፍሪቃ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በመሳተፉ ለሲኖዶሱ የአፍሪቃ ሴቶች ጉዳይ በተመለከተም ሰፊ ጥናት አዘል ንግግር ማሰማታቸውም ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.