2010-03-26 16:29:44

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በፖርቱጋል የሚደርጉት ሐዋርያዊ ግብኝት መርኃ ግብር


የፋጢማ ማርያምን ያዩ ጃሺንታና ፍራቸስኮ ብፅዕና 10 ዓመት በሚዘከርበት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በፖርቱጋል ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ባለፉት ዝግጅቶቻችን ተመልክቶ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ትናንትና ከቅድስት መንበር በወጣው ዜና መሠረት ቅዱስነታቸው እ.አ.አ. ከግንቦት 11 ቀን እስከ ግንቦት 14 ቀን በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ሊዝቦና ፋጢማና ፖርቶን እንድሚጐበኙ የቅድስት መንበር የኅትመትና የዜና ክፍል አመልክተዋል።

በአራት ቀናት ውስጥ ሶስት ከተማዎች መጐበኘት ከበድ ያለ ነው፣ ጉዞው ከፊዩሚቺኖ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ ለዘጠኝ ሰዓት አሥር ጉዳይ ይጀምራል። በ11 ሰዓት ላይ ሊስቦና ይደርሳሉ፣ የእንኳን ደህና ሥርዓት ከተደረገ በኋላ ለአንድ ሰዓት ሩብ ጉዳይ የዶስ ኸረሚኖስ ገዳምን አጠር ላለ ጊዜ ይጐበኛሉ። ከዛ በመቀጠል ከሪፓብሊክ ፖርቱጋል ፕረሲደንት ጋር ይገናኛሉ። ከቀትር በኋላ ስድስት ሰዓት ከሩብ በተረይሮ ዶ ፓኮ ሊስቦና ላይ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ። በነገታው 10 ሰዓት ላይ ከባህል ሊቃውንትናን ከፖርቱጋል ጠቅላይ ሚኒስተር ይገናኛሉ፣ ከቀትር በኋላ በሄሊኮፕተር ፋጢማ ይደርሳሉ። በዚሁ የማርያም ከተማ ብዙ ሥራ ይጠብቃቸዋል፣ አምስት ሰዓት ተኩል ማርያም የታየችበትን ቤተ ጸሎት ይገበኛሉ፣ ስድስት ሰዓት ላይ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን ኪዳን ዘሰርክ ያሳርጋሉ፣ ሰጠኝ ሰዓት ተኩል በገዳሙ ልማድ ለሚደረገው ዑደት የሚበራውን መብራት ባርከው ዑደት እያደረጉ ጸሎተ መቍጠርያን ይመራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ግንቦት 13 ቀን በደብረ ፋጢማ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ ከቀትር በኋላ ባለው ጊዜ ከግብረ ኖልዎ ማኅበሮችና ከፖርቱጋል ጳጳሳት ጋር ይገናኛሉ።
ግንቦት 14 ቀን በሄሊኮፕተር ወደ ፖርቶ በመብረር እዛ ላይ 10 ሰዓት ከሩብ በትልቁ ኣቨኒዳ ዶስ ኣልያዶስ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ። ሁሉ በሰላም ተከናውኖ ከቀትር ብኋላ ሁለት ሰዓት ላይ ከዓለም አቀፍ የከተማው አየር ማረፍያ ወደ ይበራሉ፣ በሮም 6 ሰዓት ገደማ ይመልሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከቅድስት መንበር የኅትመትና የዜና ክፍል የወጣ መግለጫ አስታወቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.