2010-03-26 16:27:25

ምእመናን ክርስቶስ እስከ ምድር ዳርቻ እንዲታወቅ ያድርጉ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ እፊታችን ጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሚታወሰው ዓለም አቀፍ የስብከተ ወንጌል ዕለት ምክንያት በማድረግ የጻፉት መልእክት ይፋ እንደሆነ ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና አመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው “የተያዝነው ዘመን በግድየልሽነት የተሸነፈ መሆኑን በመገንዘብ እያንዳንዱ ክርስትያን “መጠመቅ ማለት የወንጌል ምስክር መሆን ማለት” መሆኑን ተረድቶ የኢየሱስ መልእክትን የወንድማማችነት እርሾ በማድረግ ለዓለማችን የተስፋ ምልክት መስጠት አለበት። እንዲሁም በምጣኔ ሃብት ቀውስ የተጠቃን ብንሆንም ቅሉ ወጣት ቤተ ክርስትያኖችን መርዳት አለብን” ብለዋል።
ከዚህም ጋር በመያያዝ “የተለያዩ ባህሎችና ሃይማኖቶች የመወያየት ጥበብ ይጐድላቸዋል፣ የዓለማችን ሕዝብ ብዛት ብዙ ቢሆንም በብቸኝነት የተጥቁ አሉ፣ መልእክቶች ለማስተላለፍ ሃብታም ቢሆንም በግድየለሽነት የታመመ ነው፣ በእነዚህ ብርሃንና ጨለማ የተፈራረቀበት ሁኔታ ነው ክርስትያን በተስፋ ከፍ ማለት ያለበት፣ ይህም የሚያገኘው ደግሞ ሁኔታውን ከሚልውጠው ከኣግዚአብሔር ፍቅር ጋራ አንድ ቀን በመገናኘቱ ነው። የዚህ የታደሰ መሆን ሳቢያ ደግሞ ሰው ወንጌልን ከመስበክ ሌላ ሊሆን አይችልም።” በማለት የእያንዳንዱ ክርስትያን ጥሪ ስብከተ ወንጌል መሆኑን አመልክተዋል::







All the contents on this site are copyrighted ©.