2010-03-22 17:57:45

የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ መልእክት ለአየርላንድ ካቶሊካውያን


ወንጌልን ከኃጢኣት ይልቅ ያደበዘዙ በአንዳንድ የአየርላድ ካቶሊካውያን ቤተ ክህነት በሕጻናት ላይ የተፈጸሙ ተገቢ ያልሆነ አድራጎትን አስመልከተ ቅድስነታቸው አየርላድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የጻፍዋት መልእክት ባለፈው ቅዳሜ ይፋ ሆነች።

ቅዱስነታቸው የሁኔታውን አሳሳቢነት ሲገልጹ፣ በመልእክቱ መክፈቻ” ውድ የአየርላድ ቤተ ክርስትያን ወንድሞቼና እኅቶቼ የእንተ ላዕለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን እረኛ መጠን ይህችን መልእክት ስጽፍላችሁ ሁኔታው እጅግ ስላልሳሰበኝ ነው” ሲሉ የተፈጸመው በደል እጅግ እንደከነከናቸው የባሰው ደግሞ በቤተ ክርስትያንዋ የተወሰዱ እርምጃዎች በቂ ስላልነበሩ በግፍ ላይ ግፍ በመሆኑ በዚሁ ክህደት ከተጐዱት ምእመናን ጎን መቆማቸው ይግልጻሉ። ከዚህ ችግር ለማላቀቅ የመዳን ጉዞ በመጀመር መታደስና መካካስ ያስፈልጋል። ችግሩ የአየርላድ ቤተ ክርስትያን ወይም የመላው ቤተ ክርስትያን ልዩ ችግር ባለመሆኑ በቆራጥነትና በጽኑ ውሳኔ መጋፈጡ አስፈላጊ መሆኑንም አመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው በማያያዝ “ይህ አሳዛኝ ፍጻሜ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፈታል ብሎ ማንም እንዳይገምት፣ በሂደቱ ተስፋ የሚሰጡ እርምጃዎችም ቢወሰዱ ገና ብዙ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች ይቀራሉ፣ በአዳኙ የእግዚአብሔር ጸጋ በመተማመን ጽናትና ጸሎት ያስፈልጋሉ። ከሁሉም በላይ ግን የአርላንድ ቤተ ክርስትያን በእግዚአብሔርና በሊሎች ፊት በሚከላከል የሊላቸው ንጹሓን ሕጻናት የፈጸሙትን ኃጢአት መታመን አለባት።” በማለት የእውነተኛ ንስሐ አስፈላጊነት ካመለከቱ በኋላ ይህንን ግዝያዊና በአንዳንድ እምነተ ቢስ የቤተ ክህነት አባሎች የተፈጸመውን በደል ብቻ ሳንመለከት የአየርላንድ ቤተ ክርስትያን በስብከተ ወንጌል የከፈለችውን መሥዋዕትም ማስታወስ እንደሚያስፈልግ፣ ስንት የክርስቶስ ታማኝ አገልጋዮች ለሰው ልጆች ደኅንነትና ለስብከተ ወንጌል ሕይወታቸውን መሥዋዕት እንዳደረጉ ማስታወስም ተገቢ መሆኑን አመልክተዋል።

መልእክቱ ካህናትን በኃይል ይወቅሳል “ከንጹሓን ወጣቶችና ከቤተ ሰቦቻቸው በእናንተ ላይ የተጣለውን እምነት ክዳችኋል፣ ለዚሁ በእግዚአብሔር ፊት መልስ መስጠት አለባችሁ፣ እንዲሁም ለዚሁ ጉዳይ በቆሙ ፍርድ ቤቶችም ፊት መመለስ አለባችሁ፣ የአየርላድ ምእመናን በእናንተ ላይ ያኖረውን ክብር አጥፍታችኋል፣ ጥሪአቸውን በደምብ በተወጡ ወንድሞቻችሁ ላይም ሃፍረትና ውርደት አውርዳችኋል፣ ካህናት የነበራቻሁ የምሥጢረ ክህነት ቅዱስ መዓርግን አዋርዳችኋል፣ ከዚህም ጋር የቤተ ክርስትያንና የክህነትን መልክ አደብዝዛችኋል” ሲሉ የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን ገልጸዋል።

በመጨረሻ ቅዱስነታቸው ለሁላቸውም ለንስሐ በመጥራት “አዳኙ የኢየሱስ መሥዋዕት እስከ ትልቁ ኃጢኣት ለመማር ችሎታ አለው፣ ከመጥፎ ጥሩ ነገር ሊያውጣ ይችላል፣ በሊላ በኩል ደግሞ ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ፍትሕ እያንዳንዳችን ምንም ሳንደብቅ ጥፋቶቻችን መታመን አለበን፣ ፍትሕን መጠበቅ አለብን፣ ያም ሆኖ ይህ ግን በእግዚአብሔር ምሕረት ተስፋ መቍረጥ የለብንም” ሲሉ የበደሉ ክብደት ገልጸው እንደገና የዚህ ሰለባ ለሆኑትና ለወላጆቻቸው ቤተ ክርስትያን ይህ ዓይነት በደል እንዳይደገም ለተደረገውም ጥፋት ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ ሁሉን እንደምታደርግ አሳስበዋል።

ከወጣቶች ጀምሮ ለሁላቸውም የአየርላድ ቤተ ክርስትያን አባላት ተስፋ ሳይቆርጡ በአዲስ መንፈስ በቤተ ክርስትያን የነበራቸው መተማመን እንዲያሳድጉ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.