2010-03-22 17:59:22

ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን መንከባከብ አለብን


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና ረፋድ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት ትምህርት ነው። ቅዱስነታቸው የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰስ ይህንን ትምህርት ሰጥተዋል። ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ ዛሬ 5ኛ የዘመነ ጾም እሁድ ይዘናል፣ የዛሬው ቃለ ወንጌል ስለ በዝሙት የተግኘችውን ሴት ኢየኡስ ከሞት ቅጣት ሲያድናት እንመለከታለን፣ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 8:1-11 የተመለከትን እንደሆነ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ተቀምጦ ሕዝቡን እያስተማረ ጸሐፊዎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ሕግ ተወግራ እንድትሞት የነበራትን በምንዝርና የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጥዋት። ኢየሱስ እንዲፈርዳት ፈልገው አስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። ይህንን ያሉት ደግሞ  የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ነው። ሁኔታው እጅግ ከባድ ነው። በመጀመርያ የሴትየዋ ሕይወት በእርሱ ፍርድ ይወሰናል፣ ሊከሱትና ሊገድሉት ምክንያት ይፈልጉ ስለነበረም የእርሱም ሕይወት በሚሰጠው ፍርድ ይወሰናል። ፈሪሳውያኑ ከሳሾች ፍርድን ለእርሱ እንደሰጡ በማስመሰል ዋና ፍላጎቶቻው እሱን ለመክሰስና ለፍርድ ለማቅረብ ነው። ኢየሱስ ግን የሐንስ በወንጌሉ ምዕራፍ 1:14 እንደሚለው “በጸጋና በእውነት የተሞላ” ነው። በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ምን እንዳለ ያውቃል፣ ኃጢአትን ለመኰንን ኃጢአተኛን ለማዳን ፈሪሳውነትን ለማጋለጥ ይፈልጋል። ሰዎቹ መላልሰው እየጠየቁት ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ ቅዱስ አጎስጢኖስ ይህንን ነገር ሲፈታ በጽላተ ሙሴ ሕግን የጻፈው የእግዚአብሔር ጣት አሁንም በምድር ላይ የሚጽፈው ጣት ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮታዊ ሥልጣኑ ሕግን የሚሰጥ መሆኑን ያመለክታል ይላል። ስለዚህ ኢየሱስ ሕግ አውጪና ትክክለኛ ዳኛና ፍትሕ ራሱ መሆኑን ያመለክታል። እንታድያ ፍርዱ ምን ይሆን፣ ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት አላቸው። እነኚህ ቃላት እውነትን የመግለጽና የፈሪሳውነት ግድግዳን የማፍረስ እንዲሁም ኅሊናዎችን የሁሉም ሕግ ምንጭ ወደ ሚገኝበት ትልቁ የፍቅር ፍትሕ ይመራል። ይህ ፍትሕ የጠርሴስ ሳውልን በማዳን ወደ ቅዱስ ጳውሎስ የለወጠ ፍትሕ ነው።

ከሳሾቹ ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ከወጡ ብኋላ ኢየሱስ ሴቲቱን ከኃጢአትዋ ይፈታታል ወደ መልካም መንገድ ያቀና አዲስ ሕይወትም እንደትጀምር ያደርጋል። እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት። ቅዱስ ጳውሎስን ወደ ፍሊጵስዩስ በጻፈው መልእክቱ ምዕራፍ 3 ቍ.14 ላይ “በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።” ለማለት የገፋፋው ይህ ጸጋ ነው። እግዚአብሔር ለእኛ ለልጆቹ በጎ ነገርና ሕይወትን ነው የሚመኝልን። የነፍሳችን ጤናን ይከታተላል፣ አንድ እንኳ እንዳይጠፋ ሁላችን የመዳንን የመለወጥ ዕድል እንድናገኝ ይህንን የሚያደርገው በመልእክተኞቹ በሆኑ ካህናት በምሥጢረ ንስሐ ኃጢኣታችን ይቅር በማለት ነው። በዚሁ የካህን ዓመት ለዓመተ ካህን ባስተላለፍኩት መልእክት እንደጻፍኩት “በፍላጎቱ እኪምረን ድረስ በፍላጎቱ ኃጢኣታችንን እስከ መርሳት ራሱን በሚገፋ በመሐሪው የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲድኑ ምእመናን የምሥጢረ ንስሓ ትርጉምና ጣዕም እንዲያጣጥሙ፣ ነፍሳትን የሚንከባከቡ ካህናት የአርስ ቅዱስ ቆሞስ ምሳሌ እንዲከተሉ እማጠናለሁ።

ውድ ጓደኞቼ ሌሎችን ላለመፍረድና ላለመኰነን ከጌታችን ኢየሱስ እንማር፣ ከገዛ ራሳችን ኃጢኣት ጀምረን ኃጢአትን መቋወም ኃጢአተኛን መንከባከብ እንዳለብን መማር አለብን፣ ይህንን ለማድረግ ከኃጢኣት ሁሉ ነጻ የሆነች ቅድስትዋ የእግዚአብሔር እናትና ለተጸጸተ ኃጢኣተኛ ሁሉ ጸጋ የምታማልድ ማርያም ትርዳን፣ ብለው ካስተማሩ በኋላ የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል።

ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ እፊታችን እሁድ በዕለተ ሆሳዕና ለሚከበረው የወጣቶች ቀን በማስታወስ “በተወዳጁና በተከበሩ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከታወደ ለ25ኛ ጊዜ ለሚከበረው የወጣቶች ቀን ለመዘጋጀት ከፊታችን ሐሙስ የምሽቱ አንድ ሰዓት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አብረን እንድንጸልይ ለሁላችሁ የሮማን የላስዮ ወጣቶች ጥሪ አቀርባለሁ።” ብለዋል።

በመጨረሻም ትምህርታቸውን ለመስማትና አብረዋቸው ለመጸለይ በብዙ ሺዎች ለሚቆጠሩ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙት ነጋድያንና ምእመናን እንዲሁም በረድዮ እና በተለቪዥን ለሚከታተልዋቸው በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ችረዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.