2010-03-17 18:39:35

የር.ሊ.ጳ. የዕለተ ሮቡዕ የትምህርተ ክርስቶስ አጠቃላይ አስተምህሮ 17.02.2010


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳጳሳት በነዲክቶስ 16 ዛሬ ሮብ ረፋድ ላይ በቅዱስ ጲጥሮስ አደባባይ አጠቃላይ ሳምንታዊው የዕለተ ሮቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መክፈቻ ጸሎት አሳርገው ከመዝሙረ ዳዊት 145:8 “እግዚአብሔር ርኅሩኅና መሓሪ ነው፥ ከቍጣ የራቀ፥ ምሕረቱም ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ለሚታገሡት ቸር ነው። ምሕረቱም በሥራው ሁሉ ላይ ነው። አቤቱ፥ ሥራህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፥ ቅዱሳንህም ይባርኩሃል። የመንግሥትህን ክብር ይናገራሉ፥ ኃይልህንም ይነጋገራሉ፥ ለሰው ልጆች ኃይልህን የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቁ ዘንድ መንግሥትህ የዘላለም መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው። እግዚአብሔር በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፤ እግዚአብሔር የተፍገመገሙትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ የወደቁትንም ያነሣቸዋል። የሁሉ ዓይን አንተን ተስፋ ያደርጋል፤ አንተም ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸዋለህ። አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ። እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው። እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። ለሚፈሩት ምኞታቸውን ያደርጋል፥ ልመናቸውንም ይሰማል ያድናቸዋልም።” የሚለውን ቃለ እግዚአብሔር በኤውሮጳ ዋና ዋና ቋንቋዎች ከተነበበ በኋላ ቅዱስነታቸው ዋና ትምህርቱን በሰፊው በጣልያንኛ አቅርበዋል፣ ባጭሩም የሚከተለውን ትምህርተ ክርስቶስ ለእንግሊዘኛ ተናጋሪዎች አስተምረዋል። “ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፦ በመሀከለኛው ክፍለ ዘመን ስለነበረው የክርስትና ትምህርት የጀመርነውን በመቀጠል ዛሬም እንደገና ስለ ቅዱስ ቦናቨንቱራ እንመለከታለን። ቅዱስ ቦናቨንቱራ ከቅዱስ ቶማስ አኵናስ ጋር በአንድ ክፍለዘመን ነው የነበሩት፣ እነኚህ ሁለት ትላልቅ የንባበ መለኮት ሊቃውንት በ13ኛ ክፍለ ዘመን የነበረውን ሃብታም የንባበ መለኮት ትምህርት ይገልጻሉ። ቅዱስ ቶማስ ንባበ መለኮትን ማለት የቲዮልጂ ትምህርትን ስለ እግዚአብሔር ለማወቅ የሚረዳ ረቂቅ የሐሳብ ትምህርት መሆኑን ሊያስረዳ ሲሞክር ቅዱስ ቦናቨንቱራ ግን ንባበ መለኮት እግዚአብሔርን ለመውደድና ፍቃዱንም ለመፈጸም የሚረዳን ጥበብ የሚሰጥ ተግባራዊ ትምህርት ነው ብሎ ያስተምር ነበር። ቅዱስ ቶማስ ስለ እውነት የሚያስተምረው ትምህርት ቅዱስ በናቨንቱራ ስለ ፍቅር ከሚያስተምረው ትምህርት አንዱ ሌላውን ያምዋላል፣ ሰፊ አንድነትም ይሰጠዋል።

የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ተከታይ እንደመሆኑ መጠን ቅዱስ ቦንናቨንቱራ በቅዱስ ፍራንቸስኮስ እንድ ተገለጸለት ፍቅርን ከሁሉ ያቀድማል፣ ይህ ብቻ ሳይሆን በሰውዶ ዲዮንይስዩስ መለኮታዊ ትምህርትም ነቅቶ ነበር፣ የሰውዶ ድዮንስዩስ ንባበ መለኮት ሰማያውያን መዋቅሮች ፍጥረታት ደረጃ በደረጃ ከቅድስት ሥላሴ ጋር አንድ እንዲሆኑ ይረዳል ብሎ ያስተምር ነበር፣ የሰውዶ ዲዮንስዩስ ትምርት በአስቸጋሪው የመስቀል አስተንትኖ የተመሠረተ ነበር፣ ነገረ መስቀል እጅግ ጨለማ በመሆኑ አእምሮን ለጥቆ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ፍቅር ምሥጢር ከማስተንተን ሌላ መንገድ እንደሌለ ያስተምራል።

ትልቅ የጸሎት ሰው እንደመሆኑ መጠን ቅዱስ ቦናቨንቱራ አእምሮአችንና ልባችን ስለ ፍጥረት በማስተንተን በእግዚአብሔር ዘለዓለማዊ ፍቅር እንድናርፍ ጥሪ ያቀርብልና።

ዛሬ የቅዱስ ፓትሪክ ዝክረ በዓል በመሆኑ የአየርላድ ምእመናንን ለየት ባለ መንገድ እዚህ ያሉ ነጋድያንና ሰላም እላለሁ፣ እንደምታውቁት የአየርላድ ቤተ ክርስትያን በሕጻናት ላይ በተፈጸሙት ተገቢ ያልሆነ አድራጎት እጅጉን ተናውጣለች፣ ይህ ነገር በጥልቅ ስላሳሰበኝ ይህንን አሳዛኝ ሁኔታ በሚመለከት ሐዋርያዊ መልእክት ጽፌአለሁ፣ ከሁለት ቀናት በኋላ በቅድስት ቤተ ሰብ ጠባቂና የዓለም አቀፍ ቤተ ክርትያን ጠበቃ በሆነው ቅዱስ ዮሴፍ በዓል ፊርማኔን በማኖር እለከዋለሁ፣ ሁላችሁ በክፍት ልብና በእምነት መንፈስ እንድታነቡት አደራ እላለሁ። ይህ መልእክት፦ በሚጸመው የንስሐ፣ የመዳንና፣ የመታደስ ሂደት ይረዳል የሚል ተስፋ አለኝ። ካሉ በኋላ በቅዱስ ጲጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናንና ነጋድያንን በተለያዩ ቋንቋዎች አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት የዛሬውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.