2010-03-17 18:44:05

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንግሊዝ አገርን ይጎበኛሉ


ግርማዊነታቸው ንግሥት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ እ.አ.አ. እፊታችን መስከረም ወር ከ16 ቀን እስከ መስከረም 19 ቀን 2010 ዓ.ም. እንግሊዝ አገርን እንደሚጎበኙ ከባኪንጋም ቤተ መንግሥት የወጣ መግልጫ አስታውቀዋል።

የእንግሊዝ አገር መንግሥት እና የእስኮትላንድ እንግሊዝና ወይልስ ጉባኤ ጳጳሳት በለዶን ባደርጉት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ይህ ታሪካዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ር.ሊ.ጳ መንግሥታዊ ይፋ ጉብኝት በአገር ደረጃ ሲደረግ አንግሊካንና ካቶሊካውያን ከተለያዩ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የሚፈጸም መሆኑን ገልጠዋል። ጉብኝቱም በእንግሊዝ አገር መንግሥትና በቅድስት መንበር መሀከል ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በተመለከተ አብሮ ለመሥራትና ኃይለኛ ማኅበረ ሰቦች ለመገንባት ሃይማኖት የሚያበርከተውን ትልቅ ሚና አስፈላጊነት የላቀ ግምት ለመስጠት እጅግ አስፈላጊ መሆኑንም ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣ መግለጫ አመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው እፊታችን መስከረም 16 ቀን እንግሊዝ አገር በሚደርሱበት ግዜ ግርማዊነታቸው ንግሥት ኤሳቤጥ ሁለተኛ በአደንበራ በሚገኘው የሆልይሩድሃውስ አድራሽ ይቀበልዋቸውል። እንግሊዝ አገርን ለመጐበኘት በአገሩ ንግሥት ጥሪ የተደረገላቸው ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በወስትሚኒስተር ለእንግሊዝ አገር ሕዝብ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። በካቨትርይ ደግሞ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ በመሥዋዕተ ቅዳሴው ትልቁ የእንግሊዝ አገር የንባበ መለኮት ሊቅ የእግዚአብሔር አገልጋይ ጆን ሄንሪ ኒውማንን ወደ ብፅዕና ደረጃ ከፍ አድረገውቻዋል፣ እንዲሁም በግላስጎ መሥዋዕተ ቅዳሴ በለንደን ጸሎተ ዋዜማ ማኅሌት ያሳርጋሉ፣ የአንግሊካውያን መሪና የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳሳንም በላምበዝ ይጎበኛሉ። በጉብኝቱ መጨረሻም ቅዱስነታቸው ከሌሎች ሃይማኖቶች ተካታዮች አብረው እንደሚጸልዩም ተመልክተዋል።

የወይልስንና እንግሊዝ ጉባኤ ጳጳሳት ሊቀ መንበርና የወስት ሚኒተር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቪንሰንት ኒኮልስ ጉብኝቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ “የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝት ለመላው አገር በተለይም ለካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እጅግ አስፈላጊና ልዩ ትርጉም ያለው ነው፣ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በእንግሊዝ አገር ምን ያህል እንደምታበርክትም ሊያሳይ ይችላል፣ የአገሩ ካቶሊካውያን ይህንን የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ተልእኮ ለመደገፍ በጸሎትና በአካል ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመገኘት ሰላም እንድልዋቸውና አብረዋቸው እንዲጸልዩ” ያላቸውን ምኞት ለዚህ ተልእኮ በወጣው ድረ ገጽ ባስተላለፉት የቪድዮ መልእክት ገልጸዋል፣ የድረ ገጹ አድራሻ (/a> ) ነው። እያንዳንዳችን በመተማመንና በርኅራኄ የሕይወት እውነቶችን ለማየት ያስችለናል፣ ሲሉም ያላቸውን ተስፋ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.