2010-03-12 13:52:04

ዶሚኑስ የሱስ፦ ኢየሱስ ጌታ ነው


እ.ኤ.አ. ስኔ 16 ቀን 2000 ዓ.ም. የካቶሊክ ትምህርተ እምነት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ዶሚኑስ የሱስ በሚል እርስ ሥር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ አቻ የሌለው ብቸኛ ኵላዊ አዳኝ እና በዚህ የክርስቶስ አዳኝነት የቤተ ክርስትያን ሱታፌ ሙላት RealAudioMP3 ያለው መሆኑ የሚያብራራ ውሳኔ፣ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሒር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያጸደቁት በወቅቱ የዚህ የካቶሊክ ሥርወ እምነት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ የነበሩት ብፁዕ ካርዲናል ዮሴፍ ራትዚንገር ከር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቀጥለው የጴጥሮስ ተከታይ በመሆን የተሾሙት የቅዱስ ማኅበሩ ኅየንተ በነበሩበት ወቅት ያቀረቡት የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ድንጋጌ አሥረኛ ዓመት ምክንያት እዚህ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ረጂና አፖልቶሎሩም መንበረ ጥበብ የቲዮሎጊያ ክፍለ ጥናት ያዘጋጀው የሁለት ቀናት አውደ ጥናት ትላንትና መጀመሩ ተረጋገጠ።

አውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት የአምልኮ እና የቅዱሳት ሚሥጢራት ሥርዓት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅብረ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ካኚዛረስ ዮቨራ መሆናቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕነታችው ኢየሱስ ክርስቶስ አቻ የሌለው ብቸኛ ኵላዊ አዳኝ፣ በዚህ የማዳን ሚስጢር የቤተ ክርስትያን ሙሉአዊ ተሳትፎ በሚል ርእስ የተመራ ሥርወ እምነት በማስደገፍ ሰፊ ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ፣ ይህ ሥረወ እምነት በተመለከተ፦ አንዳንድ ገና መፍትሔ ያላገኙ ጥልቅ ጥናት የሚያስፈልጋቸው ጥያቂዎች የሚያመለክት ቢሆኑም ቅሉ አንዳንድ ጥያቄዎች ተቀባይነት የሌላቸው ከወዲሁ ስሕተት ወይንም አሻሚ የሚባሉ ናቸው ብለዋል። የሥርወ እምነት ድንጋጌ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከመውጣቱ በፊት በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 16 ከቁጥር 15 እስከ 16 “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ለሰው ሁሉ ወንጌልን አስተምሩ። ያመነና የተጠመቀ ይድናል የማያምን ግን ይፈረድብታል” በማለት ወንጌልን የማብሰር እና የማጥመቅ ተልእኮ አለበሳቸው፣ የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ከኢየሱስ ትእዛዝ የመነጨ የተሰጠ ወንጌላዊ ኃፊነት ገና ሙሉ በሙሉ ገቢራዊ መሆን ያለበት ጥሪ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በጻፋት አንደኛይቱ መልእክት ምዕራፍ 9 ቁጥር 16 “የምሥራቹ ቃል ግዴታዮ ስለሆነ የምመካበት ነገር አይደለም፣ እንዲያውም የምሥራችን ቃል ሳላበሥር ብቀር ወዮልኝ” በማለት በትክክል የዚህ የወንጌላዊ ተልእኮ ባህርይ ያስረዳናል ብለዋል።

ቤተ ክርስትያን መንገድ እውነት እና ሕይወት (ዮሓንስ 14፣ 6) የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ማበሠር ግዴታ እና ኃላፊነት አላት፣ ይህ ተልእኮ ቤተ ክርስትያን ከሁሉም ሃይማኖቶች ጋር በምታካሂደው ቲዮሎጊያዊ ውይይት የማይሻር የማይለወጥ ተልእኮ ነው። ይህ በማንም የማይሻረው ቤተ ክርስትያን ከመሥራችዋ የተቀበለቸው ጥሪ፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን የእሴቶች ቅደም ተከትል ብሎ የለም ማመን አለ ማመን ያው ነው በሚለው ኅብረ ሃይማኖታዊነት የሚያረማምድ እየተስፋፋ ባለው ባህል የተጠቃ በመሆኑም፣ የቅድስት ቤተ ክርስትያን ድንጋጌ በቅድሚያ የግልጸት ፍጻሜውን ወሳኝነቱ እና ሙላቱን ጥርት ባለ አገላለጥ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ አቻ የሌለው ብቸኛ አዳኝ ከሚለው ከዚህ ሥርወ እምነት በመነሳት፣ የክርቶስ አዳኝነት ከቤተ ክርስትያን የማይነጠል ነው። ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በጴጥሮስ ተከታይ እና በብፁዓን አቡናት ጉባኤ የምትመራ ብቸኛ (በሱታፌ የምትቀበለው ባኅርይ) የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስትያን ነች፣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መሠረት የተሾመው የጴጥሮስ ተከታይ የሮማ ሊቀ ጳጳስ ቀዳሚነት የማይቀበሉ ከከቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጋር ሙሉ ውህደት የሌላቸው አቢያተ ክርስትያን ቢኖሩም በቅዱሳት ሚስጢራት በተለይ ደግሞ በሚሥጢራት ቅዱስ ቁርባን ጥምቀት እና ሓዋርያዊ መለያ መሠረት እንዲሁም ከካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጋር ፍጹም ባይሆንም’ኳ ህብረት አላቸው ብለዋል።

የሥርወ እምነት የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር በጴጥሮስ ተከታይ ፈቃድ መሠረት የዛሬ 10 ዓመት የደነገገው የእምነት ውሳኔ ከእግዚአብሔር የማዳን ፈቃድ እና ፍላጎት ጋር የማይጻረር ነው። በክርስቶስ የማዳን ተልእኮ ሙሉ ሲታፌ ካላት ቤተ ርክስትያን ውጭ፣ ክርስቶስ ሰዎችን ሁሉ ለማዳን ባለው ፈቃድ መሠረት ድህነቱ ሊደረስ የሚቻል ነው ቢባልም በዚህ በማዳን ሚስጢር ሂደት የቤተ ክርስትያን አስፈላጊነት ድንጋጌው በሙላት ያረጋግጠዋል።

ከቤተ ክርስትያን ውጭ ድህነት የለም ሆኖም ከቤተ ክርስትያን ውጭ የሚኖሩት በጸጋው የድህነት ተካፋዮች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ጸጋ ክርስቶስ የከፈለው መሥዋዕት ውጤት በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠ ነው። ሆኖም የወቅቱ ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል ናቸው ማመንም አለ ማመንም ያው ነው የሚለው ባህል፣ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትቃወመዋለች። በርግጥ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በሌሎች ሃይማኖቶች ያለው መልካም ነገር አታገልም፣ እርሱም ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቲዮስ በጻፋት አደኛይቱ መልእክት ምዕራፍ 2 ቁጥር 4 ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን እንዲያውቁ ነው” ይኸንን መሠረት በማድረግ ከሌሎች ሃይማኖት ጋር ውይይት ታካሂዳለች፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ለመወሰን ሳይሆን፣ እግዚአብሔር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አማካኘት የገለጠው የማዳን እቅድ ሙሉ ተሳታፊነቷ ታበክራለች እንዳሉ ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.