2010-03-10 13:36:59

የአፍሪቃ ሴቶች፣ የሰላም እና የልማት መሠረት አራማጆች


ድኽነት ጦርነት የርስ በርሱ ግጭት በሽታ በሚፈራረቅባት አፍሪቃ፣ ከዚህ ዘርፈ ብዙ ችግር ትላቀቅ ዘንድ ቀዳሚ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኙት የክፍለ ዓለሟ ሴቶች መሆናቸው፣ የአፍሪቃ ህብረት ሊቀ መንበር ዣን ፒንግ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከትላትና በስትያ መጋቢት 8 ቀን ምክንያት ለመላ የአፍሪቃ ሴቶች ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩትበት ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የአፍሪቃ ሴቶች በልማት እና ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አርቆ የማሰብ በተለይ ደግሞ ለሁሉም በማሰብ ለኔ ብቻ በሚል መንፈስ ባልታጠረ ተሳታፊነት ቀዳሚው ሥፍራ ይዘው እንደሚገኙም ማብራራታቸው ተገልጠዋል።

ይህ በንእንዲህ እንዳለ፣ ትብብር እና የኤኮኖሚ ልማት የሚያነቃቃው ማኅበር በኤኮኖሚው መስክ የሴቶች ተሳትፎ በሚል ርእሰ ጉዳይ ባጠናቀረው ሰነድ የአፍሪቃ ሴቶች ተሳታፊነት 61.9 በመቶ መሆኑ በመግለጥ፣ ከሰሜኑ ዓለም እጅግ ከፍ ያለ ተሳታፊነት መሆኑም ያመለክታል።

የአፍሪቃ ህብረት ሊቀ መንበር ፒንግ ይላሉ፣ በአፍሪቃ የሴቶች ተሳትፎ የላቀ ቢሆንም ቅሉ የሴቶች እኩልነት በሙላት እንዲረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ማየል ይኖርበታል እንዳሉ ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ሴቶች በኤክኖሚ መስክ እና ለሚወጥኑትት ማኅበራዊ ሰብአዊ እና ኤኮኖሚያዊ እቅድ ማስፈጸሚያ የገንዘብ ሃብት ድርጅት እንዲቋቋም እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ በኅብረቱ ዋና ሕንጻ በተካሄደው የመሪዎች ጉባኤ መወሰኑ የሚዘከር ሲሆን፣ ፒንግ ይኸንን አቢይ አወንታዊ እርምጃ በመጥቀስ ሴቶች ከወደቁበት ችግር ለማላቀቅ በአለም አቀፍ ደረጃም ይሁን በክፍለ አለም ደረጃ ብቃት ያለው የተሟላ ትብብር ወሳኝ ነው እንዳሉ ሚስና አረጋገጠ።








All the contents on this site are copyrighted ©.