2010-03-10 13:34:24

ቅድስት ፍራንቸስካ ዘ ሮማ


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስትያን ትላትና እ.ኤ.አ. በ 1384 ዓ.ም. ተወልዳ በ 1440 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለየቸው መናንያን የቅድስት ማሪያን አገልጋዮች ደናግል ማኅበር የመሠረተችው RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. በ 1608 ዓ.ም በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ አምስተኛ ቅድስና የታወጀላት ቅድስት ፍራንቸስካ ዘ ሮማ አክብራ ውላለች።

ባለፈው ዓመት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ., በነዲክቶስ 16ኛ እዚህ ሮማ የሚገኘው የማኅበሩ ርእሰ ቤት ጎብኝተው ባሰሙት ንግግር፣ ሮማዊት ቅድስት ገና በሕጻንነትዋ ለምንኵስና ሕይወት የነበራት ጥማት በውስጧ ጎልቶ የተሰማት ጥሪ በሙላት ለመኖር የነበራት ፍላጎት ምንም’ኳ ወላጅ አባቷ ገና የ 13 ዓመት ዕድሜ ልጅ እያለች ቢድርዋትም የወላጆቿን ውሳኔ ለ 40 ዓምት አክብራ በመኖር የሦስት ልጆች እናት ለመሆን በቅታ፣ በወቅት ተከስቶ በነበረው የወረርሽኝ በሽታ ሁለት ልጆችዋ እና ባለ ቤትዋንም አጥታ ስታበቃ ዓለምን እርግፍ አድርጋ በመተው የምንኩስና ልብስ በመልበስ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 15 ቀን 1425 ዓ.ም. ያቋቋመቸው የቅዱስ ቤተዲክቶስ መንፈስ ተከታይ የደናግል ማኅበር ር.ሊ.ጳ. የውጀኒዮ አራተኛ ውሳኔ መሠረት ተቀባይነት አግኝቶ እ.ኤ.አ. በ 1436 ዓ.ም የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ በመሆን እ.ኤ.አ. በ1440 ዓ.ም.ከዚህ ዓለም ብትለይም ያስተማራቸው መንፈሳዊ ዓላማ ቀጣይነቱ ኅያው ሆኖ የእግዚአብሔር የተሰዋ ፍቅር መስካሪ እንዲሆን በቤተ ክስትያን ፈቃድ ያቋቋመቸው የደናግል ማኅበር ለቤተ ክርስትያን ለሕዝበ ግዚአብሔር አቢይ ጸጋ በመሆን አሁንም አገልግሎት እየሰጠ ነው ማለታቸው የሚዘከር ነው።








All the contents on this site are copyrighted ©.