2010-03-10 13:31:06

ቅዱስ አ.ር.ሊ.ጳ.፣ የንስሐ ተግባር


በላቲን ሥርዓት የተገባው ወደ በዓለ ትንሣኤ የሚያሸጋግረን የዓቢይ ጾም ወቅት ርእሰ በማድረግ የንስሐ ተግባር፣ በጸሎት በምጽዋት እና በጾም አማካኝነት እንደሚፈጸም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በማብራራት RealAudioMP3 ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድንፈጽም የሚያግዘን ቅዱስ መሣሪያ ነው። ሁላችን በሐጢአት ክብደት እና በሐጢአት ሰበብ በሕይወታችን የምንፈጽመው ግድፈት ሁሉ ለማራቅ የሚያግዝ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ወዳጅነት በአዲስ መንፈስ ሚያስተሳስር መሣሪያ ጾም መሆኑ እና ሌሎችን ቀርበን ለመደገፍ በቃኝ የሚለው እና ስለ ሌላው ይቅርብኝ ለማለት እንድንችል የመልካም ሳምራዊው መንፈስ በውስጥታችን እንዲያብብ ሌላው ባይተዋር እንዳልሆነ የሚያስገነዝበን ቅዱስ መሣሪያ መሆኑ እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓ.ም. የአምልኮ እና የቅዱሳት ሚሥጢራት ሥርዓት የሚንከባከብ ቅዱስ ማህበር አባላት ፊት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ማብራራታቸው የሚዘከር ነው።

እ.ኤ.አ. የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት አቢይ ጾም መግቢያ ምክንያት የሚፈጸመው የረቡዕ የሊጡርጊያ ሥነ ሥርዓት መርተው፣ ጾም የሰውነት ቅርጽ ውበት ለማስተካከል የሚፈጸም ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ውስጣዊ መንጻት እንዲጎናጸፍ በሐጢአት ያደፈውን ሰብአዊነቱን ከክፋት ለማንጻት በቃኝ የሚል ለሌላ አሳቢ መንፍስ በውስጣችን እንዲቀሰቀስ የሚያደርግ እግዚአብሔርን ለማዳመጥ ሌላውን ለማገልገል የሚያነቃቃን ቅዱስ መሣሪያ ነው ማለታቸው ከቅድስት መንበር የተላለፈ መገልጫ ያስታውሳል።

እ.ኤ.አ. የካቲት 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሮማ አቢያተ ክርስትያን ቆሞሶች ጋር በመገናኘት በለገሱት ምዕዳን፣ አቢይ ጾም፣ ቃላት ማብዛት እና በውስጣችን ከምናብሰለስለው ሀሳብ ተላቀን ውስጣዊ ጸጥታ በመላበስ፣ ከቃላት እና ከምስል ጋጋታ የሚያድነን፣ ልባችን በውስጣችን ላለው የእግዚአብሄር ምስል እና አርአያ ክፍት እንድናደርግ የሚያግዝ የተቀደሰ ወቅት ነው ብለው እንደነበር ይዘከራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.