2010-03-08 13:38:29

የወቅቱ የእምነት ሰማዕት ለመዘከር


ሮማ እና ፈረንሳይ በጋራ የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስያን እንርዳ የተሰኘው ማኅበር ያነቃቃው እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 19 እስከ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. የሚዘልቀው የወቅቱ የእምነት ሰማዕታት እንዘክር በተሰኘው መንፈሳዊ RealAudioMP3 እቅድ እንደሚሳተፉ ተገልጠዋል። ዓርብ መጋቢት 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የላተራነንሰ መንበረ ጥበብ የእምነት ሰማዕት የሆኑት ካህናት ልኡካነ ወንጌል በተመለከተ በሚቀርበው ስእላዊ እና የተቀረጸ መገልጫ አማካንነት ተጀምሮ፣ ከሰዓት በኋላ በቅዱስ ክሪሶጎኖ ባሲሊካ በሚቀርበው የመስቀል መንገድ፣ ቀጥሎ በፓኪስታን የፋይሳላባድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ጁትስ የሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚቀርብ እና ወደ ማምሻውም በመንበረ ጥበቡ በሚገኘው ቤተ ጸሎት በቅዱስ ቁርባን ፊት የእስተንትኖ እና የጸሎት ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ፊደስ የዜና አገልግሎት አረጋገጠ።

በመቀጠልም በፈረንሳይ ይህ የእምነት ሰማዕታትን ለመዘከር የሚደረገው የጸሎት መርሃ ግብር የእምነት ሰማዕትነት አሁንም እየቀጠለ መሆኑ የሚያረጋገጥ ስዕላዊ ባህላዊ ታሪካዊ መርሃ ግብር ቀጥሎ በጸሎት ሥነ ሥርዓት ተሸኝቶ እንደሚቀርብ እና በዚህ በሚካሄደው የጸሎት መርሃ ግብር የአልጀሪ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጋለብ ባደር እና የቅዱስ ቁርባን ወንድሞች ማህበር መሥራች አባ ኒኮላስ ቡተት እንደሚሳተፉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.