2010-03-08 13:33:30

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቴሌግራም መልእክት


የእስየሱሳውያን ማኅበር አባል በቻይና የመጀመሪያ ወንጌላዊ ልኡክ እና በዚህች አገር ቋንቋ እና ባህል ወንጌል የተረጎሙና የሰበኩ አባ ማተዮ ሪቺ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት 400 ኛው ዓመት ምክንያት በተለወዱባት የማቸራታ RealAudioMP3 ከተማ ስነ ምርምር፣ ስነ አመክንዮ እና እምነት፣ የአባ ማተዮ ሪቺ ሊቅነት በሚል ርእስ ሥር አውደ ጥናት መካሄዱ ተገለጠ። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዓወደ ጥናቱ መዝጊያ ዕለት ለተጋባእያን እና ለማቸራታ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ጉሊዮዶሪ የቴሌግራም መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መገልጫ አረጋገጠ።

ቅዱስነታቸው የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ ፊርማ የሰፈረበት ባስተላለፉት የቴሌግራም መልእክት፣ የአባ ማተዮ ሪቺ የባህል እና የስነ ምርምር ሊቅነት የሚደነቅ፣ ለቤተ ክርስትያን የነበራቸው የማያወላውል ፍቅር እና የአስፍሆተ ወንጌል ቅናት በነበራቸው ጥሪ መሠረት ለቻይና ህዝብ ወንጌልን በማድረስ በሕዝቡ ባህል እና ቋንቋ በማስተማር የሰጡት ሓዋርያዊ አገልግሎት የሚደነቅ መሆኑ ማብራራታቸው ተገልጠዋል።

በአውደ ጥናቱ የመክፈቻ እለት የቀድሞ የሮማ ኅይንተ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀ መንበር የነበሩት፣ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት የስነ ባህል መርሃ ግብር ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ካሚሎ ርዊኒ ባሰሙት ንግግር፣ አባ ማተዮ ሪቺ፣ ክርስትና የሚሰበክበት የህዝብ ባህል እና ቋንቋ በወንጌላዊ ባህል እዲሰበክ ለሚደረገው አስፍሆተ ወንጌል አርአያ መሆናቸው በማብራራት፣ በቻይና ቻያንዊ ሆነው ለመኖር የቻሉ ለስነ አስፍሆተ ወንጌል አዲስ ስልት ያቀረቡ አቢይ የቤተ ክርስትያን ልጅ ናቸው በማለት እንደገለጡዋቸው ከቅድስት መንበር የተላለፈ የዜና ምንጭ ያረጋገጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.