2010-03-05 13:53:58

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እና እኛ


በኢጣሊያ ሚላኖ ከተማ በሚገኘው የካቶሊክ መንበረ ጥበብ እኛ እና ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በሚል ርእስ ሥር ባዘጋጀው የሁለተኛው የቫቲና ጉባኤ በጥልቀት በዳሰሰው አውደ ጥናት ተገኝተው ሥልጣናዊ ንባበ ትምህርተ RealAudioMP3 መልኮት ያቀረቡት የካቶሊክ ትምህርት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ዣን ልዊስ ብሩገስ፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለቤተ ክርስትያን እና ለምእመናን ብቻ ሳይሆን፣ ከቤተ ክርስትያን ውጭ ለሚኖርት ጭምር የሚናገር ገና ብዙ ጥናት የሚያስፈልገው አቢይ ሃብት ነው በማለት፣ የምንኖርበት ዘመን ሊከተለው የሚገባውን መንገድ የሚጠቁም መሣሪያ ነው ብለዋል።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሌላው በቤተ ክርስትያን እንዲደመጥ ቤተ ክርስትያን ለማዳመጥ ያነቃቃ ነው ካሉ በኋላ፣ ማዳመጥን ማእከል ያደረገ ነው ሲባልም፣ የተገባ ማዳመጥ፣ ሌላውን ለማዳመጥ መንቃት እና እራስን ማዳመጥ የሚሉት ሶስት ዓለት የማዳመጥ ወይንም ጆሮን እና ልብን የመሰጠት ተግባር የሚያሰማ ነው ብለዋል።

ሃይማኖት የሚያገል ማኅበረሰብ ሳይሆን ሃይማኖትን የማይከተል አወንታዊ ዓለማዊ ምእመን ሊኖር ይችላል፣ ሆኖም ግን ሃይማኖት እንዳይኖር ጸረ ሃይማኖት መቆም የሚቻል እንዳልሆነ ገልጸው፣ የሃይማኖት ነጻነት ማለት በሃይማኖቶች መካከል ግኑኝነት እና የጋራ ውይይት ጭምር ማለት ነው ካሉ በኋላ፣ የሰላም መሠረትም ነው ብለዋል። በመጨረሻም ያቀረቡት ሥልጣናዊ ንበበ ትምህርት የአንድ ማኅበርሰብ ጤንነት መለኪያ ቤተስብ መሆኑ በመግለጥ፣ ክስትያናዊ ሰብአዊነት ጨርሶ እንዲወገድ እያደረገ ያለው በመስፋፋት ላይ ያለው የእሴቶች ደረጃ ብሎ የለም፣ ማመን እና አለ ማመን ያው ነው የሚለው ባህል ምክንያት ለአደጋ መጋለጡ እና የሰው ልጅ ሰብአዊነትን የሚሰርዝ መሆኑ ባማስረዳት፣ የማያምን ካለ አወንታዊ ዓለማዊነት አመለካከት ኖሮት ለክርስትናው ባህል ክፍት ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.