Home Archivio
2010-02-22 14:10:25
ፍቅር በሓቅ ማእከል ያደረገ አውደ ጥናት
የተለያዩ የኤኮኖሚ ሊቃውንት ያሳተፈ የሮማ ሰበካ ያዘጋጀው በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፍቅር በሓቅ በሚል ርእስ ሥር የተደረሰቸው ዓዋዲት መልእክት ማእከል ያደረገ ዓውደ ጥናት ሮማ በሚገኘው
በቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ ካቴድራል ለሁለተኛ ጊዜ መከናወኑ ተገለጠ።
አወደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት የሮማ ሰበካ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ መሆናቸው ሲገለጥ፣ በመቀጠል አስተምህሮ የሰጡት የኤኮኖሚ ሊቅ ሚላኖ የሚገኘው የቦኮኒ የስነ ኤክኖሚ መንበረ ጥበብ ሊቀ መንበር ፕሮፈሶር ማሪዮ ሞንቲ መሆናቸው ተረጋገጠዋል።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. አዋዲት መልእክት ብዙ ትኩረት የተሰጠባት እና በተለይ ደግሞ የኤኮኖሚ ሊቃውን የሳበች በተለያዩ መድረኮች የምትጠቀስ እና ለተለያዩ ስለ ኤኮኖሚ ጉዳይ በሚመለከቱት አውደ ጥናቶች ርእሰ ጉዳይ እየሆነቸው መምጣትዋም ሲገለጥ፣ ይህ በቅዱስ ዮሓንስ ዘላተርኖ የተካሄደው አውደ ጥናት እ.ኤ.አ. የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. ለተካሄደው አውደ ጥናት ቀጣይ ምዕራፍ ሲሆን፣ ሶስተኛው የአውደ ጥናቱ መርሃ ግብር እ.ኤ.አ. መጋቢት 8 ቀን 2010 ዓ.ም. የኤኮኖሚ እና የማኅበራዊ እድገት በሚል ርእስ ሥር በማተኮር እንደሚከናወንም ከወዲሁ ተገልጠዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.