2010-02-22 14:03:43

የ 2010 ዓ.ም. ጳጳሳዊ አውደ አዋርኅ

 


ባለፈው ቅድሜ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተገኙበት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ እና የቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ጠቅላላ ጉዳይ ተንከባካቢ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፈርናንዶ ፊሎኒ RealAudioMP3 በይፋ ለንባብ ማቅረባቸው ተገለጠ። ይኸንን አውደ አዋርኅ ያጠናቀሩት የቅድስት መንበር የግጽዊ ቤት ጽሕፈት ኃላፊ ፕሮፈሰር ኤንሪኮ ኔና ፊርማ የሠፈረበት ሲሆን፣ የኅትመቱ ጉዳይ ያስፈጸሙት ኣባ ፒየሮ ሚግሊዮሶ መሆናቸውም የቅድስት መንበር የዜና እና የማኅተም ክፍል ያሰራጨው መገለጫ ይጠቁማል።

ይህ አውደ አዋርህ እ.ኤ.አ. የ 2008 ዓ.ም. አኃዛዊ መሥፈርት የተከተለ መሆኑ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን የተጠናቀረው አውደ አዋርኅ የተዋጣለት ሥራ መሆኑ በመጥቀስ፣ ላጠናቀሩት እና ላዘጋጁት ምስጋና እንዳቀረቡ ተገልጠዋል።

ሚሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉ ካቶሊክ ምእመናን ብዛት አንድ ሚሊያርድ 166 ሚሊዮን መሆናቸው እና ብዛቱም በ 1.7 በመቶ ከፍ ማለት ተረጋገጠዋል። የብጹዓን ጳጳሳት ብዛት በ 1.13% ከፍ እንዳለና በተለይ ከጠቅላላው ብዛት የአፍሪቃው በ 1.83% የላቲን አሜሪካ በ 1.57% የእስያው በ 1.09% የኤውሮጳ በ 0.70% እድገት ማሳየቱ ጳጳሳዊ አውደ አዋርኅ ያመለክታል።

የሰበካ እና የገዳማውያን ካህነት ብዛት እ.ኤ.አ. በ 2000 ዓ.ም. 405.178 እንደነበር ሲገለጥ፣ በ 2007 ዓ.ም. ወደ 408.0214 እንዲሁም በ 2008 ዓ.ም. ወደ 409.166 ከፍ ማለት ለማወቅ ተችለዋል። የኤውሮጳ ካህናት ከጠቅላላው ብዛት አንጻር ሲታይ ቀንሶ መገኘቱ ተገልጠዋል። የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ብዛት በ 2000 ዓ.ም. 115.919 እንደነበር ሲገለጥ፣ በ 2008 ዓ.ም. 117.024 መድረሱም ጳጳሳዊ አውደ አዋርኅ ያረጋገጣል። እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን 169 ብፁዓን ጳጳሳት መሾማቸው ለመረዳት ተችለዋል።

የኤሺያን የዜና አገልግሎት ተጠሪ አባ በርናርዶ ቸርቨለራ ጳጳሳዊ አውደ አዋርኅ መሠረት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሚሥጢረ ጥምቀት የተቀበሉ የካቶሊክ መእመናን ብዛት ከፍ ማለት የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና የቤተ ክርስትያንዋ አባላት አገልግሎት እና ምስክርነት ኅያው መሆኑ ያረጋገጥልናል ካሉ በኋላ በአፍሪቃ እና በእስያ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች እና የካህናት ብዛት ከፍ እንዳለም ጠቅሰው፣ በነዚህ ክፍለ ዓለም ያለው እምነትን የመመስከሩ ጥማት ከፍተኛ መሆኑ የሚያረጋገጥ እድገት ነው ብለዋል።

የሃይማኖት ነጻነት እገዳ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱንም ጠቅሰው፣ ሆኖም ለሃይማኖት እድገት እና መስፋፋት አስተዋጽኦ እንዳለውም አይዘነጋም፣ መሠረታዊው ጉዳይ በደስታም ይሁን በችግር ጊዜ እምነትን መኖር ነው ብለዋል።

በኤውሮጳ እየታየ ያለው የዘርአ ክህነት ተማሪዎች እና የካህናት ብዛት ግሽበት በዚህች ከፍለ ዓለም ያለው ማመን እና አለ ማመን ያው ነው የሚለው ባህል ያጋባው መሆኑ በማብራራት፣ ስለዚህ ወንጌል ወዳልደረሰበት ወንጌልን ከማድረስ ወንጌል በደረሰበት እና ክርስትና በሆነው ባህል ለሚኖረው ከእምነት እየራቀ ላለው ሕዝብ የሚሰጠው ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እጅግ የተወሳሰበ እና ከባድ ነው ብለዋል፣ ስለዚህ በኤውሮጳ አዲስ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዲረጋገጥ የሚያሳስብ ክስተት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.