2010-02-12 11:37:11

የክብር ሊቅነት


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ ትላትና ጧት ከፖላድ ጳጳሳዊ የቲዮሎጊያ መንበር ጥበብ የክብር ሊቅነት ማእርግ በተቀበሉበት ዕለት ዴሞክራሲ እና ቤተ ክርስትያን በሚል ርእስ ሥር የቤተ ክርስትያን RealAudioMP3 ሥልጣናዊ ንባበ ትምህርት ማቅረባቸው ተገለጠ።

ብፁዕነታቸው ዴሞክራሲ እና ቤተ ክርስትያን በሚል ርእስ ሥር ባቀረቡት ንባበ ትምህርተ ቤተ ክርስትያን መሠረታውያን የሰብአዊ መብቶች ይላሉ ኵላዊነታቸው በአብላጫው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መንግሥት ወይንም የሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት እና የብዙኃን ሕዝብ አመለካከት የሚያረጋግጠው ሳይሆን፣ በሰው ልጅ መሆን ውስጥ የታተሙ በማንም የማይሻሩ እያንዳንዱ ሰው ልጅ የሚመለከት መሆኑ በማብራራት፣ ወቅታዊው ዴሞክራሲ የሕዝቦች የመራጭነት ልኡላዊነት ማለት እንደሆነ እና ዴሞክራሲ የሰው ልጅ ማእከልነት ማረጋገጫ መሆኑ ገልጠው፣ ይህ ደግሞ በቤተ ክርስትያን የሚታመንበት እና ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጭምር ዳግም በጥልቀት ያበከረው ሀሳብ ነው ብለዋል።

የሕዝብ አስተያየት እምነትን አይተካም ስለዚህ በቤተ ክርስትያን የሕዝብ አስተያየት አቢይ ግምት ቢሰጠውም ቅሉ እንደየ አስተያየቶች ምእመናን በመነጣጠል ካንዱ ማኅበርሰብ ወደ አንዱ ማኅበረሰብ የሚሸጋገሩበት እንደ አመለካከታቸው የሚሰባሰቡበት የሰልፍ ዓይነት መደራጀት አይደለም፣ ስለዚህ ከላይ ከተሰጠችው ቤተ ክርስትያን በማኅበረሰብ ወደ ምትፈጠረው ቤተ ክርስትያን ለመዘዋወር እንዲያመች ተብሎ፣ ዴሞክራሲ በጠባብ አገላለጥ በቀጥታ በቤተ ክርስያን ለማስገባት የሚደረገው ጥረት ስህተት ነው፣ ምክንያቱም የቤተ ክርስትያን መሎኮታዊ ባኅርይዋ የሚጻረር ነው። ስለዚህ በአብላጫው አስተያየት የቆመች እና በዚህ አይነቱ አስተያየት የጸናች አይደለችም ብለዋል።

ምእመናን ክርስቶስን የተቀበሉ ይኸንን እምነት በቅዱሳት ሚስጢራት የሚኖሩ የድኅነት እቅድ ለማወጅ ክርስቶስን እና ቤተ ክርስትያኑን ለመወከል ብቻ ሳይሆን የማዳኑን እቅድ በቃል እና በሕይወት ለመመስከር በክርስቶስ የተጠሩ ማለት እንደሆነ በማብራራት፣ በብፁዓን ጳጳሳት እና በምእመናን መካከል ያለው ግኑኝነት የመቆጣጠር ግኑኝነት አይደለም፣ ግኑኝነቱ ከእምነት የመነጨ የውህደት ገጠመኝ ነው ብለዋል።

ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶኔ የክብር ሊቅነት ከመቀበላቸው ቀደም በማድረግ በውሮክላው በሚገኘው የዮሓንስ መጥምቅ ካቴድራል፣ የሁሙማን ቀን የማርያም ዘ ሉድር ክብረ በዓል ምክንያት ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት፣ ዕለቱ የማርያም አማላጅነት የእግዚአብሔር አሳቢነት እና ምህረት የሚስተነተንበት ነው ካሉ በኋላ፣ ከማንኛውም ዓይነት ፍርሃት ነጻ የሚያደረገን ኢየሱስ እና ማርያም ከኛ ጋር መሆናቸው መታመናችን ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.