2010-01-29 14:15:05

ለሃይቲ ዳግመ ግንባታ


የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት አስከባሪ ዋናው የበላይ ምክር ቤት ጀነቭ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤቱ ባካሄደው የክፍለ ጉባኤ የተሳተፉት በዚህ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ሲልቫኖ ቶማሲ RealAudioMP3 በሃይቲ የተከሰተው ርእደ መሬት ያስከተለው የሰብአዊ ጉዳት እና ቀውስ ማእከል ያደረገ ንግግር ማሰማታቸው ተገለጠ።

ለሃይቲ የሚሰጠው የዓለም አቀፍ ድጋፍ ይላሉ ብፁዕ አቡነ ቶማሲ ባሰሙት ንግግር፣ በሃይቲ ለተከሰተው አስከፊው ጉዳት የሚጠግን እና የተጎዳው ህዝብ ዳግም እራሱን በመቻል ሂደት የሚያነቃቃ መሆን እንደሚገባው አሳሰበዋል። የሚሰጠው ድጋፍ በጠቅላላ አገሪቱን ዳግም ለመገንባት የሚያስችል ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ ኃላፊነት ለበስ መሆን አለበት በማለት፣ አክለውም የተለያዩ የካቶሊክ የተራድኦ ማኅበራት የሃይቲ ዳግመ ግንባታ እቅድ እያረማመዱ መሆናቸውም ጠቅሰው፣ ይኸንን በተመለከተም 160 የተለያዩ የካቶሊክ የተራድኦ ማኅበራትን የሚያቅፈው የካቶሊክ ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ማኅበር ለሃይቲ ዳግመ ግንባታ ውጥኖች ማስፈጸሚያ 33 ሚሊዮን ዶላር ማሰባሰቡ አስታውቀው፣ የአገሪቱ ሕዝብ ከደረሰበት ቁሳዊ እና ሰብአዊ ኪሳራ ለማላቀቅ ቁሳዊ ድጋፍ እና ስነ አእምሮአዊ ብሎም መንፈሳዊ ድጋፍ ጭምር እንደሚያሻው አስገንዝበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.