2010-01-27 12:47:50

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፣ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ግንቦት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በሚከበረው 44ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት፣ “ክህነት እና ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ በዚህ በአኃዝ ቅመራ ሳይንስ RealAudioMP3 እጅግ በተራቀቀበት ዘመን” በሚል ርእስ ሥር የሚያስተላለፉት መልእክት ባለፈው ቅዳሜ በቫቲካን የማስታወቂያ የዜና እና የማኅተም ክፍል አማካኝነት የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስትያን የካቶሊክ የመገናኛ ብዙኃን ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዲ ሳለስ በምታስታውስበት ዕለተ ዋዜማ ይፋ መቅረቡ የሚዘከር ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት ቀደም በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፣ ይህ ዘንድሮ በመከበር ላይ ያለው የክህነት ዓመት አቢይ ግምት የሰጠ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ክህነት እና ስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በአኃዝ የቅመራ ሥልት የሠለጠነው የመገናኛ መሣሪያ ችላ ሊለው እንደማይገባ እና የዚህ መሣሪያ ተጠቃሚ መሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በሁሉም ዘንድ እንዲታወቅ ለማድረግ መትጋት አሰፈላጊ መሆኑ በማሳሰብ፣ ውሉደ ክህነት በጠቅላላ ቤተ ክርስትያን ከዚህ አዲሱ የመገናኛ ብዙኃን መሣሪያ ጋር የጠበቀ ትውውቅ እና ተገቢ እውቀት ሊኖራት እንደሚገባም ጥሪ በማቅረብ፣ ስብከተ ወንጌል ወቅታዊ ሁኔታ የሚያነብ መሆን እንደሚገባውም ጭምር ያሳሰበ መልእክት ነው።

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መልእክት በማስደገፍ በኢጣሊያ በቶርቶና ሰበካ በሳዛኖ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ቆሞስ እንዲሁም ፖፕቱዩ የተሰኘው ድረ ገጽ አቀነባባሪ አባ ፓውሎ ፓድሪኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የቅዱስ አባታችን መልእክት እጅግ ፈጣን በሆነው አካሄድ እየተረጋገጠ ያለው ሥልጣኔ፣ በቅርብ የሚነካው ወጣቱ የህብረተ ሰብ ክፍል መሆኑ በመጥቀስ፣ ቤተ ክርስትያን ካህናት ልኡካነ ወንጌል ለነዚህ የኅብረተ ሰብ ክፍል ለየት ባለ መልኩ ትኵረት ሊስጡት እንደሚገባም የሚያሳስብ ነው ብለዋል።

ኅብረተሰባችን ይህ እጅግ በመስፋፋት ላይ ያለው የድረ ገጽ ተጠቃሚነት ጉዳይ፣ ቸል ሊባል የማይገባው እና ወጣቱ በዚህ አዲሱ ዕድገት እጅግ የተማረከ ብቻ ሳይሆን ግንባር ቀደም ተጠቃሚ ጭምር በመሆኑ፣ ለምን እና እንዴት ባለ መልኩ ሊገለገልበት እንደሚገባ ተገቢው መንገድ የሚያመለክት ነው። ቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ውልዱ ክህነት የተለያዩ የካቶሊክ መናብርተ ጥበብ፣ ወንጌል ለሁሉም ለማዳረስ ክርስቶስ በመካከላችን እንዳለ ለመመስከር እንዲጠቀሙበት ያሳሰበ፣ በቅዱሳት ሚሥጢራት ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን ከተቀበለው ከማኅበረ ክርስትያን ጋር ለመገናኘት የሚያስችል መሣሪያ መሆን እንዳለበትም ጥሪ ያቀረበ መልእክት ነው ብለዋል።

ስለዚህ ይላሉ ኣባ ፓውሎ ፓድሪኒ ይህ አዲሱ መሣሪያ ወደ ክርስቶስ የሚያቀርብ መሆን እንደሚገባው የመሰከረ መልእክት ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.