2010-01-25 13:38:46

የክህነት ዓመት


በዚህ ዘንድሮ በመታሰብ ላይ ያለው የክህነት ዓመት ምክንያት በቱርክ ካርባ ዓመት በላይ በማገልገል ላይ የሚገኙት የካፑቺኒ ማኅበር አባል ኢጣሊያዊ ካህን አባ ዶመኒኮ በርቶሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ RealAudioMP3 በቱርክ አንጽዮኪያ ክልል የሚገኘው የቅዱሳት ጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተ ክርስትያን ቆመስ መሆናቸው ከገለጡ በኋላ፣ የክህነት ጥሪያቸው ታሪክ በማውሳት የክህነት ማዕርግ እንደተቀበሉ በካፑቺን ማኅበር አለቃ ውሳኔ መሠረት በቱርክ አንጺዮኪያ ተልከው እንዲያገለግሉ ተጠይቀው ውሳኔውን በመቀበል ይኸው በአንጽዮኪያ 40 ዓመት እንደሆናቸው ገልጠዋል።

በዚህ ክልል ቆሞስ ብቻ ሳይሆኑ ከተለያይ አቢያተ ክርስትያን በሚደረገው በጋራው ውይይት እና የክርስትያኖች አንድነ እንዲረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ጭምር በመሳተፍ በዚህ ረገድም ቁምስናው አቢይ አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ጠቅሰው፣ የአንጽዮኪያ ቤተ ክስትያን አንድ ብላ የተወለደችበት ሥፍራ መሆኑም በማስታውስ፣ የቀደምት ክርስትያኖች መንፈስ የሚደመጥበት ልዩ እና ቅዱስ ሥፍራም ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በክልሉ ከሚገኙት ከኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስትያን እና እንዲሁም ከሙስሊሞች ጭምር በመከባበር ላይ የተመሠረተ መቀራረብ እንዳለም ገልጠው፣ በዚህ አካባቢ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መፈጸም አቢይ ዕድል ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.