2010-01-22 16:47:50

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አንድ ወይዘሮ ፍላሚንያ ጅዮቫኒለ የተባሉ ምእመን የፍትሕና ሰላም ርዳት ጽሐፊ እንዲሆኑ ሰየሙ፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አንድ ዶ/ር ፍላሚንያ ጂዮቫኒለ የተባሉ ምእመን በቅድስት መንበር የፍትሕማ ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ረዳት ዋና ጽሐፊ ሁነው እንዲሰሩ መስየማቸው የቫቲካ መግለጫ አስታውቀዋል።

ፍላሚንያ ጂቫኒለ በዚሁ የቅድስት መንበር ተቋም የጥናት ተባባሪ በመሆን ለበርካታ ዓመታት የሰሩ እና ያገለገሉ ምእመን መሆናቸው መግለጫው አመልክተዋል።

ምእመንዋ በ1948 እኤአ ሮማ ውስጥ የተወለዱ በሳፒየንጻ ዩኒቨርሲቲ የፖሊቲካ ሳይንስ ትምህርት ያጠናቀቁ ከ1974 ጀምረው በቫቲካን የፍትሕ እና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት በስራ ተስማርተው የነበሩ መሆናቸው የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል።

ከ2006 ጀምረው የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የአብያተ ቤተክርትያናት አገናኝ ቡድን አባል በመሆነ ውጤታማ እና አዎንታዊ አገልግሎት ያበረከቱ ምእመን መሆናቸው መግለጫው ጨምሮ ገልጸዋል።

ከአሁን በፊት የአውስራልያ ዜጋ ሮሰማሪ ጎልዲ የተባሉ ምእመን በቫቲካን የምእመናን ጳጳሳዊ ምክር ቤት ረዳት ዋና ጽሀፊ ሁነው ለበርካታ ዓመታት መስራታቸው ይታወሳል።

ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሴቶች በበኢተክርስትያን ሕይወት ሁነኛ ሚና እንዲኖራቸው ያሳስቡ መኖራቸው ይታወቃል።

ይሁን እና በቫቲካን የፍትሕ እና ሰላም ረዳት ዋና ጽሐፊ ሁነው እንዲያገልገሉ የተሰየሙት ፍላሚንያ ጂዮቫነሊ የፍትሕ እና ሰላም ረዳት ዋና ጽሐፊ ሆነው እንዲሰሩ በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሰየማቸው የተሰማቸው ጥልቅ ደስታ ገልጸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በላፈው ቅርብ ግዜ የሰባ አምስት ዕድሜ ባለጠጋ መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን ፡ የቤተክርስትያን ሕገ ቀኖና የዕድሜ ገደብ ተከትለው ዋና ጽሐፊነቱን ለርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ማስረከባቸው የቫቲካን የሃይማኖት እና ፖሊቲካ ጋዜጣ ሎሰርቫቶረ ሮማኖ ጠቁሞ ፡ ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ በዋና ጽሐፊነት እንዲቀጥሉ ሐላፊነቱን እንዳጸደቁላቸው አስገንዝበዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ የቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያረጋግጥ መልዕክት ለብፁዕ ካርዲናሉ በላኩት መልእክት እሳቸው የቅዱስ ጰጥሮስ ወኪል ማለት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከመስየማቸው በፊት ፡

በየቤተክርስትያን ተአምኖተ ሃይማኖት ቅዱስ ማኅበር ከብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ጋር በጋራ ለበርካታ ዓመታት ያካሄዱት ሐዋርያዊ ስራ ማስታወሳቸው ጋዜጣው ገልጸዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ለቤተክርስትያን ያላቸውን ሐሳቢነት እና የሰጡት አገልግሎት አሞግሰው ማመስገናቸው ጋዜጣው አስገንዝበዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.