2010-01-20 16:54:48

ለሃዪቲ የሚሰጠው ርዳታ እንደቀጠለ ነው፡


በምድር ነውጥ ህዝብዋ አብዝቶ ለተጐዳ የሃዪቲ ህብዝ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ርዳታ ባለበት እየቀጠለ መሆኑ ይታወቃል።

ባለፈው ሳምንት መጀመርያ ደሴቲቱ ላይ በተከሰተው ኃይለኛ የመሬት ነውጥ ከሁለት መቶ ሺ የመበልጡ ዜጎችዋ ለህለፈት መዳረገቸው ሁልተ መቶ ሺ መቁሰላቸው በሚልዮን የሚቆጠሩ መጠለያ አልባ መቁረታቸው ይመልከታል።

የምድር ነውጡ በደሴቲቱ ሰዓት አቁጣጠር ከቀትር በ’ኃላ አስራ ስድስት ሰዓት መከሰቱ ያስታወሰ ዜና እንደሚያመለክተው ፡ አንድ መቶ የሚሆኑ ሕጻናት ፍጹም የፈራረሰው ትምህርት ቤት ውስጥ መኖራቸው ገልጠዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰብአዊ ርዳታ አስተባባሪ ተቋም ቃል አቀባይ ኤሊዛበት ባይርስ በሕይወታቸው የተረፉ አንድ መቶ ሃያ አንድ ሰዎች ከፈራረሱት ህንፃዎች ለማዳን መቻሉ ጠቅሰው ፍለጋው እየቀጠለ መሆኑ አስታውቀዋል።

በከባድ የቁሰሉ ሰዎች በሕወታቸው ለማትረፍ የሀገራት አቀፍ ሀኪሞች በመጣደፍ ላይ መሆናቸው ቃል አባይዋ ጨምረው ገልጸዋል።

የዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት እንዳመለከተው ፡ በዋና ከተማ ፖርት ኦው ፕሪንስ ቢያንስ አስራ ሶስት ሕክምና ቤቶች በስራ ላይ እንደሚገኙ እና ፡ ለአንድ መቶ ሃያ ሺ ሰዎች ሕክምና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑ አስታውቀዋል።

የሕክምና ድርጅቱ አባላት በአደጋው ክፉኛ የቆሰሉ አንድ መቶ ሐምሳ ሰዎች እግራቸው ገሚሱ እጃቸው ለመቁረጥ መገደዳቸው የጤና ጥበቃ ድርጅቱ አስገንዝበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የርዳታ አውሮፕላኖች አፋጣኝ የምግብ እና የሚጠጣ ንጹህ ውሃ ከሰማይ በመወርወር ላይ መሆናቸው ተያይዞ ተመልክተዋል።

በዚሁ አሰቃቂ ተፈጥሮአዊ መቅዘፍት ለኃይለኛ ችግር የተጋለጠው ህዝብ በርካታ መሆኑ ተገልጸዋል።

የሃዪቲ ደሴት መንግስት መሪ ፕረሲዳንት ረነ ፕረቫል በምድር ነውጡ ለተጐዳ ህዝብ ለመዳት ዓለም አቀፍ ርዳታ በፍጥነት መድረሱ አመስግነው አሁን ርዳታውን የማቀናበር ችግር እየተከሰተ መሁኑ ገልጸዋል።

የሃዪቲ ርእሰ ከተማ ፖርት ኦው ፕሪንስ አውሮፕላን ማረፍያ የደረሰው እና በመድረስ ላይ ያለው ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ርዳታ በየአመሪካ መንግስት ባለስልጣናት እንደሚተዳደር የተገለጸ ሲሆን ፈረንሳ በዚሁ ሙያ ረገድ በሁለተኛ ደረጃ መሰለፍዋ ይመለለከታል።

ፕረሲዳንት ባራክ ኦባማ የቀድሞ የአመሪካ መሪዎች ጆርጅ ዳብልዩ ቡሽ እና ቢል ክሊንተን ለሃዪቲ የሚሰጠው ዓለም አቀፍ ርዳታ እንዲያስተባብሩ መሰየማቸው የሚታወስ ነው።

የሃዪቲ መልሶ ግንባታ ያተኮረ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተያዝነው ወር መጨረሻ ገደማ በካናዳ ሞንትርአል ላይ እንዲካሄድ መታቀዱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጠዋል።

የዓለም ባንክ ፕረሲዳንት ሮበርት ዞሊክ በሃዪቲ የተከስተው ውድመት መልሶ የተሻለ ለመገንባት ያስችላል በማለት መግለጻቸው ተነግረዋል።

ለጋሽ ሀገራት እና አገሮች አቀፍ ድርጅቶች በነውጥ የወደመውን መልሰው ለመገንባት መዘጋጀት እንደሚጠበቅባቸው የዓለም ባንክ ፕረሲዳንት ሮበር ጾሊክ አያይዘው ገለጸዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በመሬት መንቀጥቀጥ ለተጐዳው የሃቲ ህዝብ አፋጣኝ ርዳታ እየሰጠ መሆኑ እና ዘላቂ ርዳታ ለመስጠት እቅድ እንዳለው ይፋ ማድረጉ ተመልክተዋል።

ካሪታስ ኢንተርናጽዮናሊስ እና ሌሎች የቤተክርስትያን ሰብአውያን ድርጅቶች ሃዪቲ ላይ በቅድመ ግንባር ተሰልፈው አፋኛ ርዳታ እየሰጡ መሆናቸው ይታውቃል።

ከዚህ ተፈጥሮአዊ መቅስፍት የተረፈው ሃዪት ህዝብ በአሁኑ ወቅት ምግብ ንጹህ የሚጠጣ ውሃ ሕክና እና መጠለያ እንደሚያሻው ተመልክተዋል።

መጠለያ አልባ የቀረው ህዝብ ከሶስት ከሁለት ሚልዮን እንደሚበልጥ በቦታው የሚገኙ ሰብአውያን ድርጅቶች ገልጸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ በሃዪቲ ላይ የወረደው የሰው ሕይወት እና የንብረት ውድመት የተመለከቱ እና በጅጉ እንዳዘኑ የገለጹት በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ሃፈን ላይ የሚገኙ አንድ ፕሮተስታንት ሰባኪ እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል ፡ በምዕራቡ ንፍቀ ዓለም የምትገኝ ደሴት ሃዪቲ የደሴቲቱ አባቶች ደሴቲቱን ከፈረንሳ ቅኝ ግዛት ነጻ ለማውጣት ከዲያብሎስ ጋር በመስማማታቸው በዚህ የተረገመች ሁናለች።



አባባላቸው ከዓለም ዙርያ ግዙፍ ተቃውሞ ገጥሞታል ፡ ይሁን እና በብሉይ ኪዳን በእምነታቸው እና ፍትሕ አልባነታቸው የተነሳ በእግዚአብሔር እንደሚቀጡ የሚያመላክቱ ሐረጎች እንዳሉ የሚታወቅ ሲሆን አንዳንድ ክርስትያኖች እዚህ ላይ ተመርኩሰው የዓለም ሁኔታዎች ሲገልፁ ይደመጣሉ ።

ሆኖም የዛሬ ካቶሊካውያን እግዚአብሔር ራሱ ፍቅር መሆኑ በመገንዘብ ፡ እግዚአብሔር የሰው ሕጢአትን ለመግጠም የሚከተለውን አግባብ ለመረዳት የሚከትሉት አቅጣጫ ሌላ ነው።

ይህንኑ አቅጣጫ ቤተክርስትያን ሲገቡ በመንበረ ታቦት ላይ የተሰቀለውን መስቀል ማየት እና ፍቹን ማስተንተን ነው።

እግዚአብሔር የዓለም መድኅን እንዲሆን በላከው ኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በገዛ ፈቃዱ የሰው ልጅ ስቃይ ተሳፊ መሆኑ ይታወቃል እና ።

ክርስትያኖች ልብ ማለት ያለባቸው እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ወደዚ”ች ዓለም የላከው በዓለም ላይ ፍርድ እንዲበይን ሳይሆን ዓለምን ለማዳን እንደሆነ ነው።

ስለሆነም በደሴት ሃዪቲ ላይ የተከሰተው የወረደው መቅሰፍት በትክክለኛ መልኩ መረዳት በእጅጉ አስፈላጊ ይሆናል።

እንደዚህ ሃዪቲ ላይ የተከሰተው ተፈጥሮአዊ መቅሰፍት ሲደገም ይስተዋላል ፡ በዩናይትድ ስቴትስ የተከስተው ካትሪና የተሰየመው ማዕበል ፡ በኤስያ ሀገራት የታየው ሱናሚ ይተባለ ማዕበል መክሲኮ ላይ እኤአ 1985 የተከስተው የምድር ነውጥ እና ብሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ያስከተለው ውድመት ፡ ወይም በርካታ ሚእተ ዓመታት ወደ ኃላ ተመልሰን በ1775 በፖርቱጋል ሊስቦን ላይ ማዕበል እና ቃጠሎ በግንባርነት ከተማይቱን ማውደማቸው የሚታወስ ነው ።

ይህ በፖርትጋል ሊስቦን ላይ የተከስተው መቅሰፍት በእስራ ስምነተኛ ክፍለ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ቮላቴር ካንት ካርተሲዮ የተባሉ ምሁራን ዓለምን በተመለከተ የነብራቸውን አመለካከት እንዲቀይሩ አድርጎዋቸውል።

በ1755እኤአሊዝቦን ላይ ማዕበል እና የእሳት ቃጠሎ ሕብረት ፈጥረው ከተማይቱን ዘጠና በመቶ ሲያወድሙ የሁሉም ቅዱሳን በዓል ቀን ነበር የኤውሮጳ ካቶሊካውያን በእግዝአብሔር ላይ የነበራቸውን እምነት አጠያያቂ ማድረጋቸው ታሪክ ያስተምራል።

የሃዪቲ ተፈጥሮአዊ መቅሰፍት በእግዚአብሔር ያለንን እምነት እና ለከባድ ችግር የተጋለጠ ህዝብ ያለንን ርህራሔ እና ሐሳቢነት ፈታኝ ሊሆን ይችላል ።ለሁሉም ግን እግዚአብሔር ከሃሌ ኩሉ እና መሐሪ መሆኑ አንዘንጋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.