Home Archivio
2010-01-18 16:18:04
82ኛው የሮአኮ (ROACO) ጉባኤ
በሮአኮ ምሕጻረ ቃል የሚታወቀው የምሥራቅ አብያተ ክርስትያን የእርዳታ ድርገት 82ኛውን መደበኛ ጉባኤ ከዛሬ እስከ ሮብ በቫቲካን ያካህዳል።
ይህ ድርገት የተለያዩ የዓለም ተራድኦ ድርጅቶችን የሚስያስተባብር ኮሚቴ ነው። ድርገቱ በዓመት ሁለት ጊዜ እየተሰበሰበ ልዩ ትኵረት መሰጠት የሚገባቸውን አገሮችና አብያተ ክርስትያናትን እየለየ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማጥናት ይጸድቃል።
የዘንድሮ አንደኛ መንፈቅ ጉባኤ በክፍለ ዓለማችን ምሥራቃዊ ክፍል ትኵረት ያኖራል፣ በተለይም በምሥራቅና በመህከለኛ ኤውሮጳና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚገኙትን አብያተ ክርስትያን አስመልክቶ ይወያያል፣ እንዲሁም ምሥራቃዊ ሥርዓተ አምልኮ የሚከተሉትን የኤርትራ የኢትዮጵያና የኢራቅ አብያተ ክርስትያናትም ያጠቃልላል።
በጉባኤው ከህያ በላይ የሚሆኑ ከ10 የበለጸጉ ምዕራባዊ ክፍለ ዓለም የሚመጡ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የእርዳታ ድርጅቶች ይሳተፋሉ፣ እንዲሁም ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ኣቡነ አንቶንዮ ፍራንኮ የእስራኤል ሐዋርያዊ ልኡክና ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ለዮ ቦካርዲ የሱዳንና የኤርትራ ሐዋርያዊ ልኡክ፣ ይሳተፋሉ።
የዘንድሮው አንደኛ መንፈቅ ጉባኤ ዋነኛ ነጥብ “የመህከለኛ ምሥራቅና የምሥራቅ ኤውሮጳን ካህናት መርዳት” የሚለው ነው።
የቫቲካን ረድዮ የፈረንሳየኛ ቋንቋ ክፍል ኃላፊ የሆኑ ሮሚልዳ ለድርገቱ ዋና ጸሓፊ አባ ለዮ ለመንስን ጠይቀው ነበር፣ የመጀመርያው ጥያቄ ስለ የመሀከለኛ ምሥራቅና የምሥራቅ ኤውሮጳ ካህናት የገንዘብ ድጋፍ ካለፈው ለምን ዛሬ አንገብጋቢ ጥያቄ ሆነ፤ የሚል ነበር።
አባ ለዮን ለመንስ ሲመልሱ፣ “የመህከለኛና ምሥራቅ ኤውሮጳ ምሥርቃውያን ካቶሊካውያን አብያተ ክርስትያን ከሀያ ዓመታት በፊት እንደተወለዱ ማስታወስ ያስፈልጋል። በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ግን ብዙ ክህነታዊ ጥሪ በማግኘት ተባርከዋል፣ ከ3000 በላይ መዓርገ ክህነት ተቀብለዋል፣ ይህም በመሀከለኛውና በምሥራቁ ኤውሮጳ የሚገኙ የባይዛንታይን ሥርዓተ አምልኮ የሚከተሉ ቍምስናዎች እያንዳንዳቸው ቋሚ ቆሞስ አግኝተዋል ማለት ነው። ከሌላው ምዕራባዊ ኤውሮጳ የነዚሁ የተሻለ ነው፣ ሆኖም ግን የእነዚህ ካህናት ሥልጠና ብዙ ጥረት የሚጠይቅ ነበር። ሲሉ ስለ ጠቅላላው የምሥራቅ ካቶሊካውያን አብያተ ክርስትያን የክህነት ጥሪ ሁኔታ አብራርተዋል። እነኚህ አብያተ ክርትያን እንዴት እንደተወለዱ ሲገልጹም፣ “እነኚህ ኣብያተ ክርስይትያን አለምንም ውርሻ ነው ዳግም የተወለዱት፣ የኮሙኒስት መንግሥታት የነበራቸውን ሁሉ ነጠቅዋቸው፣ መንግሥታቱ ከወደቁ ብኋላ ያገኙት እርባና ቢስ ነበር። እነኚህ ኣብያተ ክርስትያን አለምንም መዋቅር ናቸው ዳግም የተወለዱት፣ ምንም ዓይነት የገንዘብ ድጋፍ አልነበራቸውም አገሮቻቸውም ድኃዎች ናቸው፣ በኡክራይና ስላለው ትልቅ የምጣኔ ሃብት ቀውስ ማሰብ በቂ ነው፣ በአመለካከታችን አገሩ አስፈላጊ ነው፣ ሁለት ሺ ካህናት አልዋት፣ ሕዝቡ ግን በረሃብና በድህነት እየተሰቃየ ነው። ይህ ማለት ባለፉት ዓመታት እነኚህ ካህናት ድጋፍ የሚያገኙት በዚሁ ድርገት ከሚሰበሰቡት የሮአኮ የእርዳታ ድርጅቶች ነው፣ ይህም ሊረጋገጥ የቻለው በምዕራቡ ክፍለዓለም ካሉ ካቶሊካውያን ግለሰቦች በሚደረግ ልግስና ነው። የምጣኔ ሃብቱ ችግር ልንገጥመው ያለብን ግብግብ ነው፣ ስለዚህ በዚሁ ጉባኤ በመሀከለኛውና ምሥራቅ ኤውሮጳ እንዲሁም ለየት ባለ መልኩ ቢሆንም በመህከለኛው ምሥራቅ ለሚገጥሙን ችግሮች መፍትሔ ለመሻት እንጥራለን፣ ብለዋል።
መሠረታዊው ጥያቄ ታድያ የትኛው ነው ለሚለው ጥያቄም እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፣ “የጥያቄው አንኳር ሕዝቡን በማገልግል ያሉትን ካህናት መንከባከብ ነው፣ ምክንያቱም ሐዋርያዊ ተልእኮቸውን በደንብ እንዲፈጽሙ የሚያስፈልጋቸውን የሚያስብላቸው ያስፈልጋል፣ እንደሃብታሞችም ይሁን እንደድሆች መኖር የልባቸውም፣ ይህ በተራድኦ ድርጅቶታችን የሚደረገው ምግባረ ሠናይ የብዙኃን ምእመናን ለዚህ ተግባር በሚሰጡት ገንዘብ የሚደገፍ ነው፣ ካሉ በኋላ ዛሬ በሠለጠነው የምዕራቡ ክፍል ብዙ ሰው ስለቤተ ክርስትያን እምብዛም በማያስብበት ወቅቱ የተራድኦ ድርጅቶቹ ገና ግብረ ሠናዩን መቀጠል የሚችሉ እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ አባ ልዮን ለመንስ “እስካሁን በድህና እየቀጠሉ ነው፣ እርግጥ ነው ባለነው ወቅት ብዙዎችን የሚያሳስብ ጉዳይ ይሄው ነው፣ ሁላቸው የሚደጋግሙት ነገር ካለም ይህ ነው፣ “እርግጥ አሁን እናደርገዋለን ሁኔታውን ያጤንን እንደሆነ ግን የዛሬ አሥር ወይም ሃያ ዓመት ልንደርገው እንችል ይሆናልን” ይላሉ። ለምሳሌ ለካህናት የሚሆን እርዳታ ከጀርመን ነው የምናገኘው፣ ይህ እርዳታ ከካህናት ነው የሚገኘው፣ ባለንበት ወቅት በጀርመን የካህናት ቍጥር እየቀነሰ ነው፣ በዚህና እላይ በጠቀስናቸው ምክንያቶች የተራድኦ ድርጅቶቹ ካህናትን የመንከባከብ ግብረ ሠናይ መቀጠሉ እያጠራጠራቸው ስለሆነ በጉባኤው ካህናቱ አለምንም ገንዘባዊ ድጋፍ እንዳይቀሩ ካሁን በግልጥ እንወያያለን ሲሉ ቃለ መጠይቁን ደምድመዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.