2010-01-13 15:06:07

ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን


እ.ኤ.አ. ጥር 17 ቀን 2010 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን የሚከበርበት ዕለት መሆኑ ሲገለጥ፣ ዕለቱን በማስመልከት የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር ጠቅላይ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ጃንካርሎ ፐረጎ RealAudioMP3 ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሕፃናት ስደተኞች ጉዳይ ማእከል ያደረገ እንደሚሆን በማውሳት፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይሁን አለ ወላጅ የተሰደዱት ሕፃናት ሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ ተሰውረው በተለያዩ የወንጀል ቡድኖች ተፍነው እንዳይሰወሩ፣ ትምህርት የማግኘት መብት ተጠብቆላቸው በጠቅላላ ልዩ ጥበቃ እንደሚያሻቸው የሚጠሩ ቅስቀሳዎች የሚከናወንበት እለት እንደሚሆን ገልጠዋል።

በተለያዩ አገሮች እንዲሁም በኢጣሊያ ስለ ስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ የተለያዩ ሕጎች ሲረቁ እና ሲጸድቁ ይታያል፣ ሆኖም ጠለቅ አድርጎ እነዚህ ሕጎች ቢጤኑ ስለ ሕፃናት ጉዳይ እምብዛም ትኵር የሚሰጡ አይመስሉም፣ ስለዚህ የነገ ተሳፋ የሆነው ትውልድ የማንኛውም የስደተኛ ጉዳይ የሚመለከት ሕግ ማእከል መሆን ይገባዋል ካሉ በኋላ፣ በጠቅላላ ስደተኛው በተስተናገደበተ አገር ለመዋሃድ እንዲችል መደገፍ አለበት፣ በተስተናጋጁም ሆነ ባስተናጋጁ መካከል መቀራረብ እና መተዋወቅ እንዲኖር አገናኝ ባህላዊ ድልድይ ማኅበራዊ እና ሰብአዊ ኅሊና ማነቃቃት ወሳኝ ነው፣ መራራቅ ካለ ስደተኛው ለዘር ልዩነት አደጋ ይጋለጣል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ደጋግመው እንዳሉት ከዚህ አይነት አደጋ ለመገላገል ስለ ሌላው ከኔ በባህልም ሆነ በሃይማኖት በቀለም ወዘተረፈ በመሳሰሉት መለያዎች የተለየ፣ የፍራት መሠረት ነው ተብሎ የሚነገርለት የማኅበራዊ ተጨባጭ ጉዳይ የማኅበራዊ እና የሰብአዊ ሃብት ምንጭ መሆኑ የሚተነትን ባህል ማነቃቃት አስፈላጊ ነው፣ ቅይጥ ማህበራዊ ኑሮ እና ጋብቻም ይሁን የፍራት እና የዘር ልዩነት መሠረት እንዳይሆን በሃይማኖት በስነ ማህበራዊ እና በባህል የተደገፍ ሕንጸት ማነቃቃት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በቅርቡ በኢጣሊያ ረጆ ካላብሪያ አውራጃ በምትገኘው የሮዛርኖ ከተማ የተቀሰቀሰው ጸረ ስደተኞች ተግባር ቀላል ግምት ሊሰጠው እንዳማይገባው የስደተኞች የድጋፍ ማኅበር ሊቀ መንበር የካፑዋ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ስኬቲኖ በመግለጥ፣ በዚህች ከተማ የታየው ውጥረት መፍትሔ በሕግ የተደገፈ ብቻ ሳይሆን በባህል የተደገፈ መሆን ይገባዋል፣ ስለዚህ ስደተኛ ማስተናገድ ሰብአዊ ግዴታ ነው። ስደተኛው ለስደት የሚዳርጉት ችግሮች መሠረታዊ መፍትሔ እንዲያገኝ መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ማኅበራት ካለ መታከት ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.