Home Archivio
2010-01-13 15:07:44
ኤውሮጳ፣ ጸረ ድኽነት ዓመት
ዘንድሮ በጸረ ድኽነት ዓላማ የኤውሮጳ አገሮች አብረው በመተባበር እና የዚህ ዓላማ የማስፈጸሚያ ውሳኔ እግርብ ላይ እንዲያውሉ በመተባበር የሚቀሰቀሱበት ዓመት መሆኑ ሲገለጥ። ዓላማው ምክንያት በማድረግም የኤውሮጳ
ብፁዓን ጳጳሳት ድኽነት ለማስወገድ ጸረ ድኽነት ውሳኔ ለማረጋገጥ የቃል ብቻ ሳይሆን የተግባር ምልከቶች ማረጋገጥ ወሳኝ ነው በማለት፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. የመላ ኤውሮጳ የጸረ ድኽነት ዕለት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሮማ የሚገኘው በካሪታስ የሚጠራው ለድኾች ድጋፍ መስጫ እና መጠለያ ማእከል በመጎብኘት እዛው በማኅበሩ ከሚደገፉ ጋር አብረው የምሳ ግብዣ እንደሚቋደሱ ሲነገር፣ የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት በዚያች ዕለት መንግሥታት ማኅበሰብ እና እያንዳንዱ ዜጋ ጸረ ድኽነት ዓላማ እግብር ላይ ያውል ዘንድ በኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት የኅብረት ድርገት ሊቀ መንበር የሮተርዳም ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አድርያኖ ቫን ሉይን እና በካሪታስ ለሚጠራው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር በኤውሮጳ ተጠሪ ኣባ ኤርንይ ጊለን በጋራ ጥሪ አቅርበዋል።
ድኽነት ለማስወገድ እና ድኾች ለመርዳት የቤተ ክርስትያን እና የማኅበረ ክርስትያን ተቀዳሚ ዓላማ መሆን እንዳለበት በማሳሰብ፣ ድኾችን ማፍቀር በእያንዳንዱ ድኻ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ማፍቀር ማለት መሆኑ በተላለፈው ጥሪ አመልክተዋል።
የኢጣሊያ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ማሪያኖ ክሮቻታ የተላለፈው ጥሪ በማስተጋባት በኢጣሊያ እና በተለያዩ የኤውሮጳ ሰበካዎች ቁምስናዎች ጸረ ድኽነት ተጨባጭ ምልክት እንዲሚቀርብ አስታውቀዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©.