2010-01-08 14:35:31

ዩሊዮስ ባሕረ ሃሳብ የሚከተሉት አብያተ ክርስትያንት


የዩሊዮስ ባሕረ ሃሳብ የሚከተሉት የምስራቅ ሥርዓት የሚከተሉት እና የኦርስቶዶክስ አቢያተ ክርስትያን ትላትና በዓለ ልደት ማክበራቸው ተገለጠ። የሞስኮ እና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል RealAudioMP3 ለበዓለ ልደት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፣ ልደት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ወደ ጌታ እንዲቀርብ ያደረገበት ቅዱስ ሚስጢር መሆኑ በማብራራት፣ በዓለ ልደት የሁሉም ሰዎች መንፈሳዊ ዳግም ልደት ያጎናጽፍ ዘንድ በመጸለይ፣ የሁሉም ልደት መሆን አለበት እንዳሉ ተገልጠዋል።

በቅዳሴው ስነ ሥርዓት የሩሲያው ርእሰ ብሔር ድሚትሪ መድቨደቭ መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ ብጹዕ ወቅዱስ ኪሪል እግዚአብሔር የሩሲያ ርእሰ ብሔር ይባርክም ዘንድ ጸልየው፣ ሩሲያ በተከሰተው ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ በጠና እንዳትጎዳ ለተለያዩ የአገሪቱ የኤኮኖሚ ዘርፍ በመደገፍ የአገሪቱ መንግሥት ያሳየው አቢይ ጥረት የሚመሰገን ነው ብለዋል።

መራሄ መንግሥት ቭላድሚር ፑቲን ከሞስኮ 300 ኪሎሜትር ርቃ በምተገኘው በኮስትሮማ ከተማ በሚገኘው ቤተ ክርስትያን ለበዓለ ልደት ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ መሳተፋቸው ተገልጠዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የልደት ሚስጢረ ብርሃን ለቤተሰብ እና ለአሕዛብ የደስታ እና የሰላም ምንጭ ይሆን ዘንድ ከትላትና በስትያ ለበአለ ግልጸት ያረገውም መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው እንዳበቁ እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገው ባስተላለፉት መልእክት በመጸለይ፣ በዚያኑ እለት በዩሊዮስ ባሕረ ሃሳብ መሠረት በዓለ ልደት ላከበሩት የምስራቅ እና የኦርቶዶስክ አቢያተ ክርስትያናት እና ምእመናን እንኳን ለበዓለ ልደት አደረሳችሁ በማለት የደስታ መግለጫ መልእክት ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው።

በኢትዮጵያ አድዋ ከተማ የሚገኙት እናቴ ላውራ ጂሮቶ የክልሉ ሕዝብ ለበአለ ልደት ያሳየው ቅድመ ዝግጅት በማድነቅ፣ በተለያዩ ምዕራብ አገሮች ይህ ዓቢይ ዕለት የገጸ በረከት መለዋወጫ የዕረፍ ቀን ብቻ እየሆነ መንፈሳዊ እና ጥልቅ ሚስጢሩ እየተዘነጋ መሆኑም በመግለጥ፣ በድኾች አገሮች የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት መሆኑ የሚያረጋገጡ መንፈሳዊ ምልክቶች ጎልተው ይታያሉ፣ የሕይወት በዓለ መሆኑ የሚገልጥ የተለያዩ ምልክቶች የሚጎላበት እለት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.