2010-01-06 12:47:06

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዓለም አቀፍ የሰላም ቀን ምክንያት ያስተላለፉት መልእክት


5. የዓለማችን የጤና ጉዳይ እና ስነ ምኅዳር እንዲሁም በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች የሚታየው የሰው ልጅ የባህል እና የግብረ ገብ መቃወስ ምልክት የአካባቢ ጤና እንዲጠበቅ ያስገዳድል። የሰው ልጅ ሥር ነቀላዊ RealAudioMP3 የባህል ኅዳሴ እና የበለጠው መጻኢ ሕይወት እንዲጸና መሠረት የሆኑትን እሴቶች ዳግም መጎናጸፍ እጅግ ያሻዋል። በአሁኑ ወቅት በዓለማችን የሚታየው የኤኮኖሚ የምግብ የአካባቢ ተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ቀውሶች የመሳሰሉት በመሠረቱ ከግበረ ገብ መቃወስ ጋር የተሳሰሩ ናቸው። ይህ ጉዳይ የጋራው ማኅበራዊ ሂደት ዳግም መወጠን እንዳለበት ግድ መሆኑ የሚያሳስብ፣ በተለይ ደግሞ እቱብ እና የተረጋጋ መተባበር ያስከተለ በአወንታዊ ገጠመኞቹ ላይ በመታመን እና በርትቶ አሉታዊ የሆኑትን ሁሉ ወስኖ በማስወገድ እና በማረም ጠለቅ ያለ አዲስ የኃላፊነት መመሪያ መወጠን እንዳለበት ያስገድዳል። እንዲህ ሲሆን ብቻ ነው ወቅታዊው የዓለማችን ቀውስ ትክክለኛ መንገድ፣ ለመለየት እና አዲስ እቅዶች እንዲወጠኑ የሚገፋፋ ጥሩ አጋጣሚ የሚሆነው።



6. ቆስሞስ በሚል ትርጓሜ ተፈጥሮ ብለን በምንጠራው ዘንድ የፍቅር እና የእውነት እቅድ እንዳለ ሓቅ አይደለምን? ዓለም የአንድ ዕውር ዕጣ ፈንታ ወይንም የማንኛውም ፍላጎት የአጋጣሚ ምርት ውጤት አይደለም፣ እግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ ከራሱ መሆን ጋር እና በርሱ መሆን ጥበብ እና ቸርነት እንዲሳተፍ ከርሱ ነጻው ፍላጎት ዘንድ ሥርወ ኅላዌ ያገኘ ነው። ኦሪት ዘፍጥረት እንደሚያመለክተውም፣ በዚህ መጽሓፍ ቀዳሚው ምዕራፎች ቆስሞስ በእግዚአብሔር የጥበብ እቅድ ዘንድ ያለ የእግዚአብሔር አሳቢነት ያፈለቀው፣ ፍጥረት እንዲገዙ ምድርንም እንዲሞሉ በእርሱ ስም እንዲያስተዳድሩ በራሱ አምሳያ እና አርአያ አድርጎ ወንድን እና ሴት ፈጠረ (ኦሪት 1 ቍ. 28)፣ ይህ በፈጣሪ በሰው እና በተፈጥሮ ዘንድ የነበረው ቅዱሳት መጻሕፍት የሚያወሱን ጥዑም ውህደት ወንዱ እና ሴቷ አዳም እና ሔዋን የእርሱ ፍጡራን መሆናቸውን ለመቀበል እምቢ ብለው የግዚአብሔርን ቦታ ለመተካት ቋምጠው በሠሩት ኃጢኣት እማካኝነት ተጥሶ፣ በዚህ አማካኝነት ደግሞ ምድርን እንዲያስተዳድሩ እንዲጠብቁ የተሰጣቸው ኃላፊነት በእነርሱ መካከል እና እንዲሁም በተቀሩት ፍጥረቶች መካከል የነበረው የተስተካከለው ግኑኝነት ተዛብቶ ግጭት ተፈጠረ (ኦሪት 3, 17 – 19)። ሰብአዊው ፍጡር እግዚአብሔር የሰጠውን ተልእኮ በማጣት በእኔነት መንፈስ ተገዝቶ፣ ተፈጥሮን በፍጹም ሙላት ለመቆጣጠር በመፈለግ ተፈጥሮን ለመበዝበዝ ተነሳሳ፣ ሆኖም በኦሪት ዘፍጥረት ተመልክቶ እንደምናገኘው እግዚአብሔር የሰጠው የቀዳሚው ትእዛዝ እውነተኛው ትርጉሙ ሥልጣናዊ ሳይሆን የኃላፊነትን ጥሪ የሚያመለክት ነው። ጥንታውያን ጥበበኞች ተፈጥሮ ለኛ የተሰጠ ነገር ግን እንደ አንድ የትርፍራፊ ጥርቅም በአጋጣሚ ተበታትኖ የተቀመጠ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ያውቁ ነበር። የቅዱስ መጽሐፍ ግልጸት ግን ሥርዓታዊ ሂደት በውስጡ ያዘለ ከዚህ አኳያም የሰው ልጅ እንዲጠብቀው እና እንዲያለማው የሚያስችለውን መንገድ ጠንቅቆ የሚለይበት ሆኖ ከፈጣሪ የተሰጠ ስጦታ መሆኑ እንድንገነዘብ አድርጎናል (ኦሪት ምዕ. 2 ቍ. 15)። ሕያው የሆነ ሁሉ ለሰው ልጅ ኃላፊነት የተሰጠ የእግዚአብሔር ንብረት እንጂ የሰው ልጅ እግዚአብሔርን በመተካት ፍርድ የሚሰጥበት አይደለም፣ የሰው ልጅ ሚና የእግዚአብሔር ተባባሪ ነው፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ለመተካት ወይንም የእግዚአብሔር ቦታ ለመጨበጥ ሲጥር ተፈጥሮን ከማስተዳደር ይልቅ ለመጨቆን ሲጣጣር የተፈጥሮ አመጽኛነትን ይጎተጉታል። ስለዚህም የሰው ልጅ ተፈጥሮን በመከላከል እና በማልማት የለማስተዳደር ኃላፊነት እንዲጠቀም ግዴታ አለበት።








All the contents on this site are copyrighted ©.