2009-12-31 17:04:37

የጣልያን ቤተክርስትያን


የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር እና የጀኖቫ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የዚህ ነገ ሐሙስ ሳላሳ አንድ ቀን 2009 እኤአ የሚጠቃለለው ዓመት መሠረት በማድረግ መግለጫ መስጠታቸው የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት መግለጫ አስታውቀዋል።

ብጹዕ ካርዲናሉ እንደገለጡት የሀገሪቱ ቤተክርስትያን እየተጠቃለለ ባለው ዓመት ከፍተኛ እንቅሳቃሴ አድርጋለች ለህዝቡ ቅርብ መሆንዋ በተግባር አሳይታለች የሀገሪቱ የሕግ ተቋሞችም ታላቅ ክብር እንዳለት አስምስክራለች ።

በማያያዝም ከሃሌ ኩሉ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረስው እና የጣልያን ቤተክርስትያን ጳጳሳት የራሱ ህዝብ እሱ በሚፈልገው መንገድ ለመምራት አግዘዋል።

በዚህ እየተገባደደ ያለውን ዓመት ለጣልያን ህዝብ እንደ በላኲላ የተከሰተው የመሬት መናውጥ እና በደቡባዊ ጣልያን በሲቺልያ ክልል በውሀ ሙላት በርካት ህዝብ ለችግር እና ለእንግልት መጋለጡ ያስታወሱት የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ቤተክርስትያን ህዝቡ ለመታደግ እና ተስፋ ለመስጠት የተቻላትን ሁሉ ማድረግዋ መግለጻቸው መግለጫው አክሎ አመልክተዋል።

ቤተክርስትያን ለችግር የተጋለጠውን ህዝብ ማተርያላዊ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ሞራላዊ እና አባታዊ ድጋፍ መስጠትዋ ያመልከቱት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ይህ ወደፊትም እንደምትቀጥልበት ማስገንዘባቸው ተያይዞ ተገልጠዋል።

ቤተክርስትያን እና የመንግስት ተቋሞች ህዝብ በተመለከተ የየራሳቸው መምርያ እና ራእይ ቢኖራቸውም ብሔራዊ ጉዳይ በተመለከተ ክአሁን በፍትም እንደ አደረጉት ሁሉ በጋራ በሰላም እና በመግባባት ሰርተዋል ወደ ፍትም በዚሁ ዓይነት አኳኅን ይቀጥላሉ የሚል ሙሉ ተስፋ እንዳላቸው ብፅዕነታቸው ማመልከታቸው ተነግረዋል።

ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት ሊቀመንበር የሕወት ክብር እና የሰው ግርማ እንዲጠበቁ ሰው ከሽል ጀምሮ እስከ መጨረሻ ሕይወት የሰው መብት እንዲጠበቅ ጽንስ ማስወረድ ወንጀል መሆኑ በመሳሰሉት ዓበይት ነገራት ቤተክርስትያን ከየመንግስት ተቋሞች ጋር መደራደርዋ እና መነጋገርዋ ቀጣይ መሆኑ አስታውቀዋል።

ሌላው ስደተኞች እና የውጭ ሀገራት ዜጎች ከሕብረተሰቡ ጋር እንዲዋሀዱ የሚል የቤተክርስትያን ተቋም በካታ የፖሊቲካ ሰዎች ሐሳቡ ውድቅ በማድረግ ቤተክርስትያን ሲወቅሱ እንደሚሰሙ ያስታወሱት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ የቤተክርስትያኒቱ አቋም ግን ይሄው ነው ማለታቸው የጣልያን ረኪበ ጳጳሳት መግለጫ አስገንዝበዋል።

በአጠቃላይ የኤውሮጳ ህዝብ በተለይ የጣልያኑ ክርስትና ብሎም ካቶሊካዊነት መንነቱ እና ባህሉ መሆኑ ተገንዝቦ እንዲራመድ ያሸዋል በማለት ብፅዕነታቸው ማመልከታቸ ተንግረዋል።

ሌላው በዚሁ እየተጠቃለለ ያለውን ዓመት 2009 እኤአ የጣልያን ቤተክርስትያን ራስዋ እና ከተቋሞችዋ ጋር በመተባበር በዓለም ዙርያ ለሚያጋጥሙ የመሬት መናወጥ የውሃ ሙላት ሌሎች መቅሰፍቶች ሁነኛ ርዳታ አቅርባለች ይህ ሰብአዊ እና ሰናይ ተግባርም ትቀጥልበታች

በማለት ብፁዕ ክርዲናል ባኛስኮ እስገንዝበዋል ።

ሰብአውያን መብቶች እንዲከበሩ የክርስትያን እሴቶች እንዲጠበቁ እመኛለሁ ያሉት ብፁኦ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በመጨረሻም ከነገ ወድያ ዓርብ የተያዝነው ዓመት 2009 የሚተካውን 2010 እኤአ የሰላም እና የብልጽግና ዓመት ይሆን ዘንዳ መመኘታቸው መግለጫው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.