2009-12-18 14:26:06

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የመሩት ጸሎተ ሠርክ


ሁሌ በየዓመቱ እደሚደረገው በሮማ የሚገኙት የመናብርተ ጥበብ ተማሪዎች ከሌሎች የኤውሮጳ እና ከኤውሮጳ ውጭ የተወከሉ የመናብርተ ጠብብ ተማሪዎች ለበዓለ ልደት ማዘጋጃ በሦስተኛ ሳምንት ምክንያት ትላትና RealAudioMP3 በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመሩት ጸሎተ ሰርክ ተሳትፈዋል።

የዚህ በየዓመቱ የሚደረገው የቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. እና ተማሪዎች ግኑኝነት በ 2000 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ለተማሪዎች መርኅ ትሆን ዘንድ የሰጡት የመንበረ ጥበብ ቅድስት ድንግል ማሪያም ምስል ያስቀደመ መሆኑ ሲታወቅ፣ ይህች በሁሉም አገሮች ዑደት እንደምታደርግም ሲገለጥ፣ ዘንድሮ በአውስትስራሊያ ዑደት እንደምታደርግ እና በዚህ ምክንያት በጸሎቱ ስነ ሥርዓት የተገኙት የአውስትራሊያ መናብርተ ጥበብ ተማሪዎች ልኡካን መሰጠቱም ተገልጠዋል።

የሮማ ሰበካ የመንበረ ጥበብ ተማሪዎች ሐዋርያዊ ኖልዎ ተንከባካቢ ምክር ቤት ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ሎረንዞ ለውዚ ስለ ተካሄደው በዓል አስመልክተውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በየአመቱ ር.ሊ.ጳ. እና ተማሪዎች የሚያካሂዱት የግኑኝነት በዓል በመስዋዕተ ቅዳሴ የሚከናወን እንደነበር አስታውሰው፣ ዘንድሮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመሩት ጸሎተ ሰርክ መከናወኑ ባለፉት ዓመታት ከተከናወኑት ግኑኝነቶች ለየት አድርጎታል ካሉ በኋላ፣ ዘንድሮ የመናብርተ ጥበብ ተማሪዎች የሚከተሉት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ቅዱስ ቁርባን እና ትህትና የተሞላው እውቅት በሚል ርእስ ሥር የሚመራ መሆኑ አውስተው፣ በዚህ በተካሄደው ግኑኝነ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እምነት እና ምርምር በሚል ርእስ ሥር የሰጡት አስተምህሮ ይኸንን የዘንድሮው የግብረ ኖልዎ መርሃ ግብር በጥልቀት ያስረዳ ነበር ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.