2009-12-16 13:54:59

ኅያዋን የክርስቶስ መስክሮች


እ.ኤ.አ ከታህሳስ 29 ቀን 2009 ዓ.ም. እስከ ጥሪ 2 ቀን 2010 ዓ.ም. በፖላንድ ፖዝናን ከተማ የተዜ መንፈሳዊ ማህበረሰብ ለሚያካሂደው 32ኛው ዓለም አቀፍ የሁሉም ሃይማኖት ወጣቶች ጉባኤ ምክንያት ቅዱስ አባታችን RealAudioMP3 ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መልእክት ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፣ የቁስጥንጥንያ ፓትሪያርክ ብጹዕ ወቅዱስ በርጠለሚዮስ አንደኛ እና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የበላይ መንፈሳዊ የካንተር በርይ ሊቀ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ ተመሳሳይ መልእክት ማስተላለፋቸው ለማወቅ ተችለዋል።

ቅዱስ አባታችን እና እንዲሁም በኤውሮጳ የሚገኙት የሌሎች ሃይማኖቶች መንፈሳዊ መሪዎች ያስተላለፉት መልእክት፣ በኤወሮጳ ወጣት ላይ ያላቸውን እምነት የሚያረጋገጥ እነዚህ ወጣት የኤውሮጳ ህብረተሰብ አባላት በዓለም የተስፋ ምስክሮች እንዲሆኑ የሚያሳስብ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት የቫቲካን ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሮበርቶ ፒየርማሪኒ እንደተነተኑት፣ ቅዱስነታቸው የተዜ የሁሉም ሃይማኖቶች መንፈሳዊ ማኅበረሰብ በፖዝናን ከተማ በሚያካሂደው ጉባኤ እንዲሳተፉ ያቀረበላቸው ጥሪ በመጥቀስ በጸሎት እና በመንፈስ እደሚያብሩ ማረጋገጣቸው እና በዚህ መንፈዊ ሃያምኖታዊ ሁለ ገብ ጉባኤ የሚሳተፉ አማኒያን ወጣቶች፣ በዓለማችን በሕይወታቸው የእግዚአብሔር ኅላዌ ችላ በማለት የእግዚአብሔር ትርጉም በማግለለል የራሳቸው ጭምር አግለው የሚኖሩት የሕይወታቸው ትርጉም ለመሻት የሚዋልሉት እና የኅላዌ መልኅቅ በማጣት በዘልማድ እንዲሁ የሚኖሩትን የዓለማችን ወጣቶች እና በያንዳንዱ ሰው ዘንድ ያለው እግዚአብሔርን የመሻት መንፈስ የሚያነቃቃ በእግዚብሔር ላይ የጸናው እምነታቸውን እንዲመሰክሩ አደራ ሲሉ፣ ጳጳስ ሮዋን ዊሊያምስ በበኩላቸውን ባስተላለፉት መልእክት የዓለም ማኅበረሰብ በሐሰት ሃይማኖቶች ተታለው በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ ርእዮት ላይ የነበራችው ተስፋ ወድቆ ምንኛ መቁሰሉ እና መበርገጉንም ጠቅሰው፣ ክርስቶስን መከተል የእምነት እሴቶች እግብር ላይ በማዋል በምሰጡት የፍቅር ምስክርነት በመማረክ እንድታጽናኑ የእምነታቸሁን ሐሴት መስክሩ ብለዋል።

ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርጠለሚዮስ አንደኛም አማኒያን ወጣቶች ኅያዋን የኅልዎተ ክርስቶስ መስካሪያን ሁኑ እንዳሉ ጋዜጠኛ ፒየርማሪኒ ካቀረቡት ትንታኔ ለማረጋገጥ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.