2009-12-14 14:33:35

የምጽአት ሳምንት ሶስተኛው እሁድ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በላቲን ሥርዓት የኃሴት እሁድ ተብሎ በሚጠራው በሶስተኛው የምጽአት እሁድ፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ፊሊጲሲዩስ ሰዎች በጻፋት መልእክት ምዕራፍ 4 ከቁጥር 4 እስከ 5 “የጌታ በመሆናችሁ ሁሉ ጊዜ ደስ ይበላችሁ፣ ደግሜም የምላችሁ ደስ ይበላችሁ ነው። ምሕረት የተሞላበት ደግነታችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ RealAudioMP3 የታወቀ ይሁን ጌታ ሊመጣ ቀርቦኣል” የሚለውን የጌታ ቃል መርህ በማድረግ ክርስትያን ደስተኛ ሰው ማለት ነው፣ ምክንያቱም የምጽኣት ጊዜ በመሆኑ ጌታ ሊመጣ ቀርቦአል፣ የጌታ መምጣት መቃረብ የኛ የደስታ ምንጭ ነው። እግዚአብሔር መምጫው ተቃርቦአል በሚለው ቃል ያለው ክርስትያናዊ እርግጠኛነት መሠረት በማድረግ፣ እግዚአብሔር ቅርባችን ነው ከኔ፣ ካንተ እና ከኛ ጋር ነው፣ እግዚአብሔር ወደ ሰው ይመጣል በእርሱ የሚታመን እርሱን መከታው የሚያደርግ ደስ ይሰኛል ብለዋል።

በዚህ የፍጆት ባህል በገነነበት ወቅታዊው ዘመን፣ በንግዱ ዓለም ብቻ የተመራ ሰው ገዥ ደንበኛ ብቻ አድርጎ የሚመለከተው ባህል፣ የደስታ ምንጭ ሊሆን አልቻለም፣ ውጫዊ ደስታ በውስጣችን ከመንፈስ ሙላት የሚገኘውን እውነተኛው ደስታ በመተካት የሰው ልጅ የተረበሸ የተዋከበ እንዲሆን አድርጎታል። በእግዚአብሔር ፋንታ የግል ደስታ ብቻ በመሻት የሚደረገው ሩጫ ያለህን ሁሉ በማፍሰስ ሊጨበጥ የሚፈለገው ደስታ የሰውን ልጅ ለተለያዩ አደጋዎች አጋልጦት ይገኛል፣ ይህ ደግሞ የሰው ልጅ ባዶ በማስቀረቱ ምክንያት ባዶነቱን ለመሙላት የአደንዣዥ እጸዋት መጠቀም ተገሎ መኖርን እኔነትን እያስፋፋ የሚፈለገውን ደስታ በማራቅ ሰውን በማታለል ሐዘንተኛ እንዲሆን አድርጎታል። እውነተኛው የደስታ ምንጭ እዚአብሔር ነው ብለዋል።

እ.ኤ.አ. ታህሳስ 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን የእግዚአብሔር መቃረብ፣ የቦታ እና የጊዜ ጥያቄ ሳይሆን የፍቅር ጉዳይ ነው፣ ፍቅሩ ይቀርባል፣ የሚለው እምነታችን የሚያረጋገጥልን እውነት ሁሌ በማስታወስ ጌታ በፍቅሩ ሊጎበኘን ሥጋችንን ለብሶ ወደኛ ይመጣል በመካከላችንም ይሆናል እንዳሉ የሚዝከር ነው።







All the contents on this site are copyrighted ©.