2009-12-11 14:36:47

ተፈጥሮ የመንከባከብ ኃላፊነት


በተፈጥሮ ላይ የሚከሰተው ብከላ እና ዓለማችን የሚከተለው የእድገት ስልት በተፈጥሮ የአየር ንብረት ላይ የሚያስከትለው ብከላ ለማስወገድ ምን መደረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ በመስጠት እና የሚሰጠው ምላሽ ውሳኔ RealAudioMP3 በማድረግ እግብር ላይ ለማዋል የተጠራው በኮፐንሃገን በመካሄድ ላይ ያለው የተባበሩት መንግሥታ ድርጅት ያነቃቃው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ባራተኛው የውይይት ቀን በበለጸጉት እና በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች መካከል የጦፈ ክርክር መታየቱ ሲገለጥ፣ የዴንማርክ መንግሥት ሁለቱንም ወገኖች ለማግባባት የሚያስችል ሃሳብ ማቅረቡ እና የቀረበው ሓሳብ ርእስ በማድረግ ውይይት መካሄዱ ተረጋገጠዋል።

ተፈጥሮ ከብከላ አደጋ ለማዳን ለመስማማት ካልሆነም አንድ የጋራ መመሪያ ለመከተል ግድ መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ ውሳኔ ባስቸኳይ እግብር ላይ ካልዋለ ብከላው እየባሰ ለማስወገዱ የሚጠይቀው ውጪ ከፍ እያለ እንደሚሄድ ጉባኤው አስምሮበታል። የበለጸጉት እና በማደግ ላይ የሚገኙት አገሮች ይኸንን ጠባብ እድል ችላ ሊሉት እንደማይገባም ተበክረዋል።

በማደግ ላይ የሚገኙት አገሮች ውስጥ በእድገት ጎዳና ከፍ ብለው የሚገኙት አገሮች በጋራ ብከላውን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ያስችላል ያሉት አንድ ሰነድ ማቅረባቸው ሲገለጥ፣ ገና የሰነዱ ይዞታ በይፋ ባይገለጥም፣ የክዮቶው የስምምነቱን ሰነድ መሠረት በማድረግ የበለጸጉት አገሮች እ.ኤ.አ. እስከ 2020 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ የአየር ንብረት በካይ ጋዝ ለማጉደል የተደረሰው ስምምነት እግብር ላይ ይውል ዘንድ የሚጠራ መሆኑ ሲገለጥ፣ በዚሁ ረገድ ቻይና የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት አቢይ ሚና ይጫወት ዘንድ ስታሳስብ፣ ያም ሆኖ ይህ የዋሽንግተን መንግሥት እስከ 2020 ዓ.ም. ባለው የጊዜ ገደብ ውስጥ በካዩ ጋዝ በ 17% ለማጉደል እቅድ እንዳለው በይፋ ሲያስታወቅ፣ የኤውሮጳ ህብረት እስከ ተጠቀሰው የዓመታት ገደብ ውስጥ በካዩን ጋዝ በ 30% ለማጉደል መወሰኑ አስታውቀዋል።

በዚህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ በተባበሩት መንግሥታት ለቅድስት መንበር ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ቸለስቲኖ ሚሊዮረ፣ ይህ ጉባኤ በበለጸጉት አገሮች እና በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች መካከል ያለው የሃሳብ ልዩነት እጅግ የጎላበት መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ጠቅሰው፣ ቅድስት መንበር ሁሉም ተፈጥሮ በመንከባከብ ያለውን ኃላፊነት በማነቃቃት ይኸንን ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት አስፈላጊ እርምጃ እንዲረጋገጥ እያሳሰበች ነው ብለዋል። የሚወጠኑት እቅዶች በማደግ ላይ የሚገኙት አገሮች እግምት ውስጥ ያስገባ እና እቅዱን በመከተል ረገድ የሚነካው ኤኮኖሚያቸው በበለጸጉት አገሮች ሊደገፍ ይገባዋል ካሉ በኋላ፣ ተፈጥሮ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ ነው ስለዚህ እንክብካቤ እና በሚገባ ማስተዳዳር የሁሉም ኃላፊነት ነው፣ እድገት እና ተፈጥሮን መንከባከብ እና በሚገባ የማስተዳደር ጥሪ ማዛመድ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ጉባኤ በይፋ ከመከፈቱ በፊት ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተፈጥሮ ያየር ንብረት ላይ የሚረጨው በካይ ጋዝ ርእሰ አድርጎ መወያየት ስለ ተፈጥሮ መናገር ማለት መሆኑ ገልጠው ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ጸጋ መከላከል ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር በሰጠን ኃላፊነት መሠረት መንከባከብ ይኖርብናል ያሉትን ሀሳብ ብፁዕ አቡነ ቸለስቲኖ አስታውሰው፣ ተፈጥሮን ለመከባከብ የሚያስችለው ውሳኔ የመውሰድ ዓቢይ ኃላፊነት ያለባቸው አገሮች ሁሉም በመተባበር ለዚህ ዓላማ መቆም ይኖርባቸዋል ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.