2009-12-11 14:38:04

ስለ እግዚአብሔር የሚመለከቱ ጥያቄዎች


እግዚአብሔር ዛሬ፣ ከርሱ ጋር እና አለ እርሱ ሁሉም ይቀየራል የሚል ጥያቄ ርእስ በማድረግ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያነቃቃው ዓቢይ ቲዮሎጊያዊ እና ፍልስፍናዊ አውደ ጥናት ትላትና ሮማ በሚገኘው የአውዲቶሪዩም የጉባኤ አዳራሽ መከፈቱ ተገለጠ።

የቲዮሎጊያ እንባ የፍልስፍና ሊቃውንት ጋዜጠኞች ምሁራን RealAudioMP3 የባህል አካላት የመናብረተ ጥበብ አስተማሪዎች የፖሊቲካ አካላት፣ ስለ እግዚአብሔር ጥያቄ በማንሳት እየተወያዩ መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ ጥያቄ በሙዚቃ በግጥም በስነ ጽሑፍ በሳይንስ በተለያዩ የስነ ጥበብ መድረኮች የሚነካ እና የሚነሳም ሲሆን፣ አውደ ጥናቱ የኢጣሊያ የብጹዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ እና የሮማ ከተማ ከንቲባ ጃኒ አሌማኖ ለተጋባእያኑ ባሰሙት የሰላምታ መልእክት መጀመሩ ተገልጠዋል።

በጉባኤው እግዚአብሔር በተመለከተ የሰው ልጅ የሚያቀርበው ጥያቄ በቲዮሎጊያ እና በፍልስፍና በመዳሰስ ንግግር ያሰሙት የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ሊቀመንበር የነብሩት ብፁዕ ካርዲናል ካሚሎ ርዊኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ሕይወት በባህል ባህል ደግሞ በሕይወት ላይ የተደገፈ ነው። ይህ በባህል እና በሕይወት መካከል ያለው የመደጋገፍ ሂደት፣ በሁለቱም ዘንድ ያለው ጥልቅ ግኑኝነት የሚያመለክት ሲሆን በባህሉ መድረክ የክርስትና ኅላዌ ለአስፍሆተ ወንጌል ወሳኝ ነው ብለዋል።

አስፍሆተ ወንጌል የልብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ባህሎችን በጥልቀት የሚነካ የሚጠይቅ የባህል መሠረቱን የሚያናጋ መሆን ይገባዋል፣ ስለዚህ ስሜታዊ ብቻ ሳይሆን ስነ ጥበባዊ ጭምር ነው ብለዋል። ብዙውን ጊዜ ባህሎች ከዚህ ጥያቄ ለመሸሽ ሲራወጡ ይታያል፣ ሆኖም ለመሸሽ የሚያደርግ ሩጫ መልሶ ወደ መሠረታዊው ጥያቄ ፊት እንዲቆሙ ያደርጋቸዋል፣ ስለዚህ ክርስትና ባለው ጥልቅ ባህል መሠረት ከባህሎች ጋር የሚወያይ ነው ብለዋል።

የዓለማውያን ምእመናን እሰይታ አበክሮ ያሳሰበው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ዓለማዊ ምእመን በማህበራዊ እና በፖሊቲካ መድረክ በቀላሉ የሚሳተፍ በመሆኑም፣ የክርስትናው ባህል በሚገባ በቃል በሕይወት ለመመስከር ተጠርተዋል። በእግዚአብሔር ለማመን እግዚአብሔርን ለመቀበል እና በመጨረሻም ቤተ ክርስትያን የምታቀርበው የስነ ሃይማኖት ትምህርት እና አንቀጸ ሃይማኖት በመቀበል እምነትን በሙላት መኖር አስፈላጊ ነው። በእግዚአብሔር አምናለሁ ብሎ ብቻ መቅረቱ እግዚአብሔር መቀበልን አያረጋግጥልንም፣ መወለድ እና መሞት የሕይወት መጀመሪያ እና መደምደሚያ አይደለም ይህ ደግሞ እውነተኛው እና ሓቀኛው ክርስትና የክርስቶስን ትምህርት መሠረት በማድረግ የሚያስተምረው ትምህርት ነው፣ ክርስቶስ ለራሱ ሲል ብቻ አይደለም የተነሳው፣ ስለ ሁሉም ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.