2009-12-09 15:38:13

በኢጣሊያ የቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ጉብኝት


እ.ኤ.አ. 2010 ዓ.ም. ቅዱስ አብታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ በኢጣሊያ ሰበካዎች የሚያካሂዱት ሓዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር መቅረቡ ተገለጠ። ትላንትና እንተ ላእለ ኵሉ ቅድስት ቤተ ክርስትያን በዓለ ጽንሰታ RealAudioMP3 ለማርያም ባከበረችበት ዕለት ሐዋርያዊ ጉብኝት በሚያካሂዱባቸው ሰበካዎች ለምእመናን በይፋ ተገልጠዋል።

በወጣው መርሃ ግብር መሠረትም፣ እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2010 ዓ.ም. ቶሪኖን ቀጥለውም ሐምሌ 4 ቀን በሳልሞና መስከረም 5 ቀን 200ኛው የር.ሊ.ጳ. ለዮነ 8ኛ ዝክረ የልደት ዓመት ካርፒነቶ ሮማኖ የሚጎበኙ ሲሆን፣ ጥቅምት 3 ቀን 2010 ዓ.ም. የሲቺሊያ የቤተሰብ እና የወጣቶች ጉባኤ ምክንያት ፓሌሮሞን እንደሚጎበኙ የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.