2009-11-30 14:06:02

የሕፃናት መብት እና ፈቃድ ጥበቃ


እ.ኤ.አ. እፊታችን ጥር 17 ቀን 2010 96ኛው አለም አቀፍ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ቀን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ምንም’ኳ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕጻናት መብት እና ፈቃድ ጥበቃ ውሳኔ RealAudioMP3 የተደነገገ ቢሆንም ቅሉ፣ አሁንም የብዙ ስደተኛ ሕፃናት ሕይወት ላደጋ ተጋልጦ እንደሚገኝ በማሳሰብ፣ ሕፃናት በሁሉም አለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲከበሩ እና እንዲጠበቁ ማሳሰባቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ስለ ሕፃናት ጉዳይ በተመለከተ በኢጣሊይ ለሕፃናት አድን ድርጅት ተጠሪ ቫለሪዮ ነሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ር.ሊ.ጳ. ያስተላለፉት መልእክት ሁሉን መንግሥታት እና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ለሕፃናት መብት እና ፈቃድ መከበር ይተጉ ዘንድ የሚያሳስብ ከመሆኑም ባሻገር፣ ሕፃናት የማይከበሩበት ዓለም ለጥፋት የተጋለጠ መሆኑ የሚያስረዳ ነው ካሉ በኋላ፣ መንግሥታት በቅድሚያ የሁሉም በተለይ ደግሞ የሕፃናት መብት እና ፈቃድ በማክበሩ እና እንዲከበር በማነቃቃቱ ኃላፊነት ሊነቁ ይገባል። ከዚህ በመነሳት ማኅበርሰብ ይኸንን ውሳኔ እንዲያከብር ማሳሰብ እና ማነጽ ይቻላል። ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ስደተኛ እና ተፈናቃይ ሕፃናት አለ እውቅና እየቀሩ ለተለያዩ አደጋ ተጋልጠው ስታይ የሚዘገንን ነው፣ ስለዚህ ስደተኞች ሕፃናት በጥገኝነት በሚገኙበት አገር የተሟላ ድጋፍ አግኝተው በሚገባ ተስተናግደው ለመኖር የሚያስችል እድል ሊረጋገጥላቸው ተገቢ ነው ብለዋል።

ሕፃናት ስደተኞች ለተለያዩ አደጋ ሲጋለጡ ይታያል፣ እንዳውም ተሰውረው የት እንደገቡ ሳይታወቅ፣ መሰወራቸው እና መጥፋታቸውን የሚያጋልጥ ክስ የሚያቀርብም ባለ መኖሩ ይኸው ብዙ ሕፃናት በተለያዩ የወንጀል ብዱኖች ወጥመድ ሥር ወድቀው ይገኛሉ፣ ስለዚህ ይኸንን አሰቃቃዊ በሕፃናት ላይ የሚፈጸመው ዘግናኝ በደል እንዲሁም የመብት እና የፈቃድ ረገጣ ሁሉም መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ማህበርሰብ በጋራ ሊዋጉት ይገባል ብለው፣ ሕፃናት በመንከባከብ ኃላፊነት ሁሉም እንዲሳተፍ አደራ ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.