2009-11-28 09:36:15

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ የቺለና አርጀንቲና መሪዎች ተቀብለው እንደሚያነጋግርዋቸው ተገለጸ፡


ነገ ቅዳሜ ታህሳስ ሀያ ስምንት ቀን እኤአ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ አስራ ስድስተኛ ሁለት የላቲን አመሪካ ሀገራት መራህያነ መንግስታት የቺለ መንግስት ፕረሲዳንት ሚሸል ባችለት እና የአርጀንቲና መንግስት መሪ ክሪስቲና ፈርናንደጽ ኪርሽነር ተቀብለው እንደሚያነጋግሩ የቫቲካን መግለጫ አስታውቀዋል።

የሁለቱ ላቲን አመሪካ ሀገራት መግስታት ቫቲካን ጉብኝት ዋነኛ አላማ እኤአ በ1984 ሁለቱ ሀገራት ለጦርነት ተዘጋጅተው ተፋጠው በነበሩበት ግዜ ቫቲካን በአስታራቂነት ጣልቃ በመግባት ጦርነቱ እንዲገታ ያደረገችበት እና ሀገራቱ የሰላም ስምምነት የተፈራረሙበት ሀያ አምስተኛ ዝክረ ዓመት መሠረት ያደረገ መሆኑ የቫቲካን መግለጫ አስገንዝበዋል ።

የመንግስታቱ መሪዎች ቅድስት መንበር ማለት ቫቲካን ያካሄደችው የዲፕሎምሲ ጥረት እና አለመግባባቱ በሰላም እንዲቀረፍ ያደረግችው ደግ ሙያ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለማመስገን ትኩረት የሰጠ መሆኑም ነው የቫቲካን መግለጫ ያመለከተው።

ቺለ በጀነራል አውጉስቶ ፒኖሸ አርጀንቲና በጀነራል ኾርኸ ቪደላ ይመሩ በነበሩበት ግዜ በካናል ቢግል የሚገኙ ተጓራ`ባች ደሴቶች ልዓላውነት በተመለከተ ጦር ለመማዘዝ መዘጋጀታቸው የሚታወስ ነው ።

ሁለቱ ተጓራባች የላቲን አመሪካ ሀገራት ብሰላማዊ እና አትላንቲክ ውቅያኖሶች ለማለፍ ከፍተኛ ስትራተጂ ያላቸው የቢግል ካናል ተጓራባች ደሴቶች ለኔ ይገባሉ የለም በሚል ቅራኔ ተዋጥረው መኖራቸው የሚታወስ ነው ።

በቫቲካን አስታራቂነት ውጥረቱ እንደተገታ ሰላማዊ ድርድር አካሄደው የሰላም ስምምነት እንደተፈራረሙ የደሴቶቹ ልዓላውነት በሰላም ለቺለ እንደተሰጡ እና ሀገራት ዩነታቸው አስወግደው ሰላማውያን እና ተባበረው የሚኖሩ መለካም ጐረቤቶች መሆናቸው የማይዘነጋ ነው።

ቫቲካን በወቅቱ በቺለ እና አርጀንቲና መካከል የተከሰተው ፍጥጫ ለመርገብ እና ሁለቱ ሀገራት ልዩነታቸው አስወግደው የሰላም ስምምነት እንዲፈራረሙ ባታደርግ ኖሮ በሁለቱ ሀገራት የሰው ሕይወት እና ንብረት ኪሳራ ማስከተሉ የማቀር መኖሩ መግለጫው አስታውሰዋል።

ቺለ እና አርጀንቲና ውጥረት ለማርገብ እና ብሎም ሰላም እንዲሆን ቫቲካንን ወክለው በአስታራቂነት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ሳሞረ እና አሁን በብሪታንያ የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ፋውስቲኖ ሙኞጽ እንደነበሩ የቫቲካን መግለጫ አመልክተዋል።

ብፁዕ አቡነ ፋውስቲኖ ሙኞጽ በዚያውኑ ግዜ ሁለቱ ሀገራት ለማስታረቅ የተካሄደውን የዲፖሎማሲ ጥረት አስታውስው እንዳመለከቱት ፡ሁለቱ ሀገራት እንደተፋጠጡ የሀገራቱ መሪዎች እግዚአብሔር አማክሮአቸው በወቅቱ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንዲሸመግልዋቸው ሐሳብ ማቅረባቸው ገልጸዋል ።

ነፍሰሄር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊም በፍጥነት በብጹዕ ካርዲናል አንቶንዮ ሳሞረ የሚመራ አስታራቂ ቡድን ወደ ሁለቱ ሀገራት መላካቸው ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ፋውስቲኖ ሙኞጽ ፡

የሁለቱ ሀገራት አለመግባባት ሰላማዊ መፍትሔ ለመሻት በአገሮች አቀፍ ማኅበረ ሰብ እና በተለያዩ መንግስታት ሙከራ ተካሄዶ ባለ መሳካቱ በመጀመርያ ደረጃ የተፈለገውን ውጤት

ባያስከትልም የቫቲካን አስታራቂ ቡድን ጉዳዩ ጠብቆ በመያዝ እና ግዜ ሳይፈጅ ከመንግስታቱ ጋር በመደራደር የሰላም ፍንጭ ማግኘቱ ፡ብሎም ሰላም ማስፈን መቻሉ ራሳቸው የቫቲካን አስታራቂ ቡድን አባል የነበሩት አሁን ባታላቅ ብሪታንያ የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ወኪል ብፁዕ አቡነ ፋውስቲኖ ሙኞጽ አብራርተዋል።

የቺለ እና አርጀንቲና የይገባኛል ውጥረት ለማርገብ እና ሰላም ለማስፈን ሁነኛ ሚና የተጫወቱ ከበርካታ ዓመታት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ብፁዕ ካርዲናል አንቶንዮ ሳሞረ መኖራቸው ብፁዕ ኣአቡነ ፋውስቲኖ ሙኞጽ መስከረዋል።

ባለፈው ስምንት በቺለ ርእሰ ከተማ ሳንትያጎ ደል ቺለ ካቶሊካዊ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲ እና በቺለ የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ቺለ እና አጀንቲና የሰላም የትብብር እና የወዳጅነት ስምምነት የተፈራረሙበት ሀያ አምስተኛ ዓመት በድምቀት መከበሩ እና እሳቸውም የዚሁ የሰላም እና ዕርቅ ዝክረ ዓመት መገኘታቸው እና ህዝቡ እና የሀገሪቱ መንግስት በስምምነቱ እጅግ እንደተሰተ ለማስተዋል እና ለመራዳት መቻላቸው ብፅዕነታቸው ገልጸዋል።

ማንኛውም ውዝግብ የሰው ሕይወት ሳያልፍ እና ንብረት ሳይወድም በሰላማዊ ድርድር መፍትሔ ለማግኘት እንደሚቻል የቺለ እና አርጀንቲና መልካም አርአያ መሆኑ ፡ ብፁዕ አቡነ ፋውስቲኖ ሙኞጽ አስገንዝበዋል ።








All the contents on this site are copyrighted ©.